በሸዋሮቢት ሳላይሽ ላይ 9 አሸባሪዎችን በመግደል በክብር የተሰውት ጀግና አባት እና ልጅ _እሸቴ ሞገስ እና ይታገስ እሸቴ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 1 ቀን 2014 ዓ.ም……

በሸዋሮቢት ሳላይሽ ላይ 9 አሸባሪዎችን በመግደል በክብር የተሰውት ጀግና አባት እና ልጅ _እሸቴ ሞገስ እና ይታገስ እሸቴ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 1 ቀን 2014 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ህዝብ ሕልውናው ይረጋገጥ ዘንድ ብሎም መብት፣ጥቅምና ፍላጎት ይከበር ዘንድ አያሌ ጀግኖች አሸባሪዎችንና ወራሪዎችን በመደምሰስ ክብር መስዋዕትነት ከፍለዋል፤ እየከፈሉም ይገኛሉ። ቀወት የተወለዱት የሸዋው ጀግና ኑሮአቸውን በሸዋሮቢት አድርገው ከህዝቡ ጋር ከፍ ባለ ተሰሚነትና ክብር በፍቅር ይኖሩ ነበር። አሸባሪውና ወራሪው የትሕነግ ቡድን ወደ ሸዋሮቢት ሲገባ ለጠላት አልሸሽም በሚል በእናታቸው ተማጽኖ ከምሽጉ ተነስተው ወደ ሳላይሽ ከእነ ልጃቸው ሄደዋል። ወራሪዎቹ ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ/ም ሳላይሽ ላይም በተመሳሳይ ተኩስ ከፍተውባቸዋል_አባት እና ልጅም 9 የሚሆኑትን እንዳይመለሱ አድርገው ሸኝተዋል_ከአፈር ጋር ቀላቅለዋል። ለባንዳ መሸሽን እንደ ሞት የቆጠሩት ጀግኖቹ ባንዳን ይዞ የጀግና ሞት መሞትን፣ በደም እና አጥንታቸው የማይሞት ታሪክ መጻፍን መርጠዋል፤ ጀግኖቹ ጠላትን ከረፈረፉ በኋላ ተሰውተዋል። ቀድሞ የተሰዋው ልጅ ይታገሱ እሸቴ ነበር፤ አባት አቶ እሸቴ ሞገስ ልጄን ጥዬ፣ ቀዬዬን ጥዬ መሸሽ አይታሰብም አሉ። ስልክ ደውለው ታሪካዊ መልዕክትም አስተላለፉ፤ እስከ መጨረሻው ድረስ ወራሪን እንደሚፋለሙ አረጋገጡ፤ ከልጃቸው ጎን እንደሚወድቁም ተናገሩ፤ የወዳጃቸውን ምክርም ለመስማት አልፈለጉም፤ ቃላቸውን አከበሩ_ስለወገንና ስለሀገር ነጻነትና ክብር ሲባል ከጀግናው ልጃቸው ይታገሱ ጎን ጀግናው አባታችን እሸቴ ተሰው። ጀግናው ሸዋ መላው አማራ ተዋርዶ መሞትን መጠየፉ፣ ባንዳን ፊት ለፊት አጋድሞ ለክብሩ መሞት ከጥንት ጀግኖቹ የወረሰው ነው። ሸገር ኤፍ ኤም የጀግናው እሸቴ ሞገስን ታሪካዊ ስልክ ልውውጥ ባያያዘበት ዘገባው የሚከተለውን አስፍሯል:_ ኢትዮጵያ ነፃነቷ ጸንቶ፣ታፍራና ተከብራ የቆየችው ደማቸውን ባፈሰሱላት፣ አጥንታቸውን በከሰከሱላት የቁርጥ ቀን ጀግና ልጆቿ አማካይነት ነው፡፡ ይህ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ ጀግንነት፣ አልደፈርም ባይነት ዛሬም ከሳምንታት በፊት በሸዋሮቢት አጋጥሟል፡፡ ሕወሃት ለወረራ በሸዋሮቢት፣ በሳላይሽ በገባበት ወቅት አካባቢዬን አላስደፍርም ብሎ ከአሸባሪዎች ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው 9 በመግደል መስዋዕት ጀግና አባትና ልጆች ስለወገን ሲባል ራስን አሳልፈው የሰጡ ፋኖነታቸውን፣ አርበኝነታቸውን አጉልተው ያሳዩ ጀግኖች ናቸው። ስለወደቀው ፤ የሆነውንም ሀገር ይወቀው፣ ልጆቼንም አደራ ብለዋል!_ እሸቴ ሞገስ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply