You are currently viewing በሸዋሮቢት ሳላይሽ ላይ 9 አሸባሪዎችን በመግደል በክብር የተሰውት ጀግና አባት እና ልጅ እሸቴ ሞገስ እና ይታገስ እሸቴ! ታህሳስ01/2014/አሻራ ሚዲያ/ የአማራ ህዝብ ሕልውናው ይረጋገጥ ዘ…

በሸዋሮቢት ሳላይሽ ላይ 9 አሸባሪዎችን በመግደል በክብር የተሰውት ጀግና አባት እና ልጅ እሸቴ ሞገስ እና ይታገስ እሸቴ! ታህሳስ01/2014/አሻራ ሚዲያ/ የአማራ ህዝብ ሕልውናው ይረጋገጥ ዘ…

በሸዋሮቢት ሳላይሽ ላይ 9 አሸባሪዎችን በመግደል በክብር የተሰውት ጀግና አባት እና ልጅ እሸቴ ሞገስ እና ይታገስ እሸቴ! ታህሳስ01/2014/አሻራ ሚዲያ/ የአማራ ህዝብ ሕልውናው ይረጋገጥ ዘንድ ብሎም መብት፣ጥቅምና ፍላጎት ይከበር ዘንድ አያሌ ጀግኖች አሸባሪዎችንና ወራሪዎችን በመደምሰስ ክብር መስዋዕትነት ከፍለዋል፤ እየከፈሉም ይገኛሉ። ቀወት የተወለዱት የሸዋው ጀግና ኑሮአቸውን በሸዋሮቢት አድርገው ከህዝቡ ጋር ከፍ ባለ ተሰሚነትና ክብር በፍቅር ይኖሩ ነበር። አሸባሪውና ወራሪው የትሕነግ ቡድን ወደ ሸዋሮቢት ሲገባ ለጠላት አልሸሽም በሚል በእናታቸው ተማጽኖ ከምሽጉ ተነስተው ወደ ሳላይሽ ከእነ ልጃቸው ሄደዋል።… ወራሪዎቹ ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ/ም ሳላይሽ ላይም በተመሳሳይ ተኩስ ከፍተውባቸዋል_አባት እና ልጅም 9 የሚሆኑትን እንዳይመለሱ አድርገው ሸኝተዋል_ከአፈር ጋር ቀላቅለዋል። ለባንዳ መሸሽን እንደ ሞት የቆጠሩት ጀግኖቹ ባንዳን ይዞ የጀግና ሞት መሞትን፣ በደም እና አጥንታቸው የማይሞት ታሪክ መጻፍን መርጠዋል፤ ጀግኖቹ ጠላትን ከረፈረፉ በኋላ ተሰውተዋል። ቀድሞ የተሰዋው ልጅ ይታገሱ እሸቴ ነበር፤ አባት አቶ እሸቴ ሞገስ ልጄን ጥዬ፣ ቀዬዬን ጥዬ መሸሽ አይታሰብም አሉ። ስልክ ደውለው ታሪካዊ መልዕክትም አስተላለፉ፤ እስከ መጨረሻው ድረስ ወራሪን እንደሚፋለሙ አረጋገጡ፤ ከልጃቸው ጎን እንደሚወድቁም ተናገሩ፤ የወዳጃቸውን ምክርም ለመስማት አልፈለጉም፤ ቃላቸውን አከበሩ_ስለወገንና ስለሀገር ነጻነትና ክብር ሲባል ከጀግናው ልጃቸው ይታገሱ ጎን ጀግናው አባታችን እሸቴ ተሰው። ጀግናው ሸዋ መላው አማራ ተዋርዶ መሞትን መጠየፉ፣ ባንዳን ፊት ለፊት አጋድሞ ለክብሩ መሞት ከጥንት ጀግኖቹ የወረሰው ነው። ሸገር ኤፍ ኤም የጀግናው እሸቴ ሞገስን ታሪካዊ ስልክ ልውውጥ ባያያዘበት ዘገባው የሚከተለውን አስፍሯል:_ ኢትዮጵያ ነፃነቷ ጸንቶ፣ታፍራና ተከብራ የቆየችው ደማቸውን ባፈሰሱላት፣ አጥንታቸውን በከሰከሱላት የቁርጥ ቀን ጀግና ልጆቿ አማካይነት ነው፡፡ ይህ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ ጀግንነት፣ አልደፈርም ባይነት ዛሬም ከሳምንታት በፊት በሸዋሮቢት አጋጥሟል፡፡ ሕወሃት ለወረራ በሸዋሮቢት፣ በሳላይሽ በገባበት ወቅት አካባቢዬን አላስደፍርም ብሎ ከአሸባሪዎች ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው 9 በመግደል መስዋዕት ጀግና አባትና ልጆች ስለወገን ሲባል ራስን አሳልፈው የሰጡ ፋኖነታቸውን፣ አርበኝነታቸውን አጉልተው ያሳዩ ጀግኖች ናቸው። ስለወደቀው ፤ የሆነውንም ሀገር ይወቀው፣ ልጆቼንም አደራ ብለዋል!_ እሸቴ ሞገስ።ምንጭ አሚማ

Source: Link to the Post

This Post Has One Comment

  1. Tesfa

    የታለ የሴቷ ፎቶ። ሴቶችን ማስቀደም አስፈላጊ ሆኖ እያለ በዜናም ሆነ በጦር ሜዳ ላይ በሚደረጉ ቃለ መጠይቆች ሁሉ ወንዶች ብቻ ሲናገሩ እናያለን። ይህ መቆም አለበት። የሴት ቁርጠኛ ወገኖቻችን መዘከር፤ መድመቅ፤ መታወቅ አለባቸው። ምግብ ከማዘጋጀት ጀመሮ እስከ ጦር ሜዳ ውሎ ያለውን ያጠቃለለ ዘገባ ያስፈልጋል። አብረው ታጥቀው በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ እያደሩ፤ በውሃና በረሃብ እየተጎድ ለሃገራቸው የሚታገሉትንና የተሰውትን በግልጽ ማስታወቅ አለብን። ይህ ሴቶችን ወደ ኋላ የመግፋት ባህላችንም ሆነ ሃይማኖታዊ እይታችን አሽቀንጥረን ልንጥለው የሚገባ ነገር ነው።
    እነዚህ ቤተሰቦች የትግራይ ወራሪ ሃይልን ለመፋለም ያደረጉት ጀብድ የሚዘከር ነው። ልክ እንደ እነዚህ ጀግኖች ሁሉም ተደራጅቶ ገና ከጅምሩ ቢፋለማቸው ኑሮ ሽዋ ለመድረስ ባልቻሉም ነበር። ህዝባችን ሰልጥኖ፤ ታጥቆ፤ ተደራጅቶና ተግባብቶ፤ አንድን ለአንድ ተደራሽ በሚያደርግ ሁኔታ ካልተሰባሰበ ይህ የወያኔ ጥቃት በአንድና በሌላም ጊዜ ሊደገም ይችላል። የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ የወሬ ዘጋቢዎችን ፈቃድ በመስጠት የትግራይ ወራሪ ሃይሎች ያደረሱትን በደልና መከራ እንዲዘግቡ ለምን እንደማያደርግ አይገባኝም።፡ ሌላው የሚገርመኝ ነገር ከቪዲዪ ይልቅ በትክክል የተነሱ ፎቶዎች ብዙ ይናገሯል። የደረሰው በደል ሁሉ በፎቶ ቢዘገቡ ለታሪክም ሆነ አሁን ላለው መረጃ አሰባሰብ ጠቃሚ ናቸው። አሁን እንሆ ወያኔ በአንዳንድ ቦታዎች እየተዋጋ መሆኑን እያነበብን ነው። ያለ የለለ ሃይልን በማሰባሰብ እጃቸውን ካልሰጡ ማውደም መቻል አለበት። በፍጽም ቀን ሊሰጠው አይገባም። ተበትኖ፤ ተቆርጦ ገለ መሌ የሚለውን ወሬአችሁን ተውን። ወያኔ ለሰላም እምቢኝ ብሎ እልፍ ሰዎችን እንዳስለቀሰ እሱም አፈር መቅመስ አለበት። የማይደን ድውይ ሃሳብ የተጠናወተው የድርቡሾች ጥርቅም ነውና። የተማረኩ፤ ታስረው የሚገኙ የትግራይ ሰዎችን በአውቶብስ አሳፍሮ መቀሌ ላይ ወስዶ መጣል ነው። የናፈቃቸው የትግራይ ሪፕብሊክን መመስረት ከሆነ ይመስርቱና እዚያው ይኑሩ። አብረን በሰላም እንኑር ሲባሉ አልሰሙንምና። ወያኔን ከሥር መሰረቱ ነቅሎ ሊያጠፋ የሚችለው የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው። በቃኝ!

Leave a Reply