አርብ ሰኔ 30 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ)
በሰሜን ሽዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር አንድ የፖሊስ አባል ትላንት ምሽት በሥራ ላይ እያለ ባልታወቁ አካላት መገደሉን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
የተገደለው የፖሊስ አባል ምክትል ሳጅን ያለለት ደጉ ሲሆን፤ በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር 08 ቀበሌ ከምሽቱ አራት ሰዓት በሥራ ላይ እያለ ባልታወቁ ግለሰቦች በጥይት ተመትቶ መገደሉን ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
ከሦስት ቀን በፊት የከተማ አስተዳደሩ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አብዱ ሁሴን በተመሳሳይ ባልታወቁ አካላት በጥይት ተመተው መገደላቸውን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል፡፡ በከተማዋ በተደጋጋሚ መሰል ጥቃቶች የሚፈጸሙበት ሁኔታ እየተሰማ ሲሆን፣ በተለይ የፌደራል መንግሥት መከለከያን በአካባቢው ካሰማራ በኋላ ችግሩ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡
Source: Link to the Post