You are currently viewing በሸዋሮቢት ከተማ አንድ የፖሊስ አባል በስራ ላይ እያለ መገደሉ ተገለጸ።      አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሰኔ 30/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ምክትል ሳጅን ያለለት ደጉ የተባለ…

በሸዋሮቢት ከተማ አንድ የፖሊስ አባል በስራ ላይ እያለ መገደሉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሰኔ 30/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ምክትል ሳጅን ያለለት ደጉ የተባለ…

በሸዋሮቢት ከተማ አንድ የፖሊስ አባል በስራ ላይ እያለ መገደሉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሰኔ 30/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ምክትል ሳጅን ያለለት ደጉ የተባለ የፖሊስ አባል ሰኔ 29/2015 ማታ በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር 08 ቀበሌ ከምሽቱ 4 ስዓት በስራ ላይ እያለ ባልታወቁ ግለሰቦች በጥይት ስለመገደሉ ተገልጧል፡፡ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ሰኔ 27/2015 ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ ከቢሮአቸው በሚወጡበት ሰዓት ማንነቱ ባልታወቀ አካል ተተኩሷል በተባለ ጥይት ተመተው መገደላቸውን ተከትሎ ጊዜያዊ የጸጥታ ኮማንድ ፖስት ከሰኔ 28/2015 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከምሽቱ 12 ስዓት ጀምሮ:_ ማንኛውም ተሽከርካሪ ይሁን የሰው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የተገደበ ነው። አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የምሽት ክለቦችን ጨምሮ ከምሽቱ 12 ስዓት በኋላ ምንም አይነት አገልግሎት አይሰጡም በማለት እጅግ ገዳቢ ክልከላ ማወጁ ብዙዎችን ያስቆጣ መሆኑ ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply