በሸዋሮቢት የገቢዎች ጽ/ቤት ሠራተኛ የነበረች ግለሰብ በጥይት ተመትታ ህይወቷ አለፈ፡፡የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የሥራ ባልደረባ የሆነችው ጽዮን ተገኝ ትላንት ምሽት 12 ሰ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Yf7ZfMCHV27kBERK0-Lb1EqrV42vCPxGVLqfbfmtOBG9hh1Hi6jIeiuvKNv0ZIX8LWj09phMYoGzK3f5foJAdnlW5EBvZLORrQFRCEHi7A1wlM_X3YREJInL2uLu-tl1ZeFn3pnnrvHfSIAk5y6ZBUDP7iB6Z98JM9qK1m6oSumVswVN1p03fR1DZgWmSceSV6HqSSRHTOErovH0wQlUFpqaQ5w8_c-u1u0w-i98FsEfWXdYW-vhicVDHIjtQXVVS8K-N3EUZS0xwNj_M1hhzR6DqkBC908rGhIhdijZxMOAKGl9axKncR6KLJRDs3A_RjLibjVh2uTZmGJdTvZSjw.jpg

በሸዋሮቢት የገቢዎች ጽ/ቤት ሠራተኛ የነበረች ግለሰብ በጥይት ተመትታ ህይወቷ አለፈ፡፡

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የሥራ ባልደረባ የሆነችው ጽዮን ተገኝ ትላንት ምሽት 12 ሰዓት አካባቢ አቅጣጫው ካልታወቀ ቦታ በተተኮሰ ጥይት ሕይወቷ ማለፉን የከተማ መስተዳድሩ አስታውቋል፡፡

ግለሰቧ ቤተሰብ ለመጠየቅ በባጃጅ ላይ እያለች በተተኮሰ ጥይት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን፤ ግድያዉ ተጣርቶ ወንጀለኞችን በህግ ቁጥጥር ሥር ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳድር ባወጣዉ የሀዘን መግለጫ ተናግሯል።

ከተማ አስተዳደሩና መላው ሠራተኛ በጽዮ ህልፈተ ህይወት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ፤ ለወዳጅ ዘመዶቿ እንዲሁም ለቤተሰቦቿ መጽናናትን ለሟች ደግሞ ነፍሷን በአጸደ ገነት እንዲያኖርልን እንደመኛለን ብሏል፡፡

በሸዋሮቢት ከዚህ ቀደም የከተማዋ ተቀዳሚ ከንቲባ የነበሩት ዉብሸት አያሌዉ በተመሳሳይ ጥቃት ህይወታቸው ማለፉ አይዘነጋም።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ህዳር 14 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply