በሸዋ ለደራ ወረዳ በክልል ተፈቅዷል የተባለ ደረጃውን የጠበቀ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተመልሶ መከልከሉ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 13 ቀን…

በሸዋ ለደራ ወረዳ በክልል ተፈቅዷል የተባለ ደረጃውን የጠበቀ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተመልሶ መከልከሉ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 13 ቀን…

በሸዋ ለደራ ወረዳ በክልል ተፈቅዷል የተባለ ደረጃውን የጠበቀ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተመልሶ መከልከሉ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ለደራ ወረዳ ተፈቅዷል የተባለው ደረጃውን የጠበቀ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ባላወቅነው ምክንያት እድሉ መታጠፉና ለሌላ ተላልፎ መሰጠቱ ቅር አሰኝቶናል ያሉ የደራ ወረዳ ነዋሪ ተወካዮች ቅሬታ ለማሰማት አዲስ አበባ ድረስ መጥተዋል። መሬታችን ለግንባታ ውሰዱ ያሉ ሰዎችን ጨምሮ 16 የሚሆኑ የሀይማኖት አባቶችና የማህበረሰቡ ተወካዮች ወደ ሰሜን ሸዋ ዞን ፊቸ በማቅናት ጥያቄያቸውን ለትምህርት ጽ/ቤት ቢያቀርቡም በጎ ምላሽ አለማግኘታቸውን ነው የገለፁት። ለአንድ ሳምንት የህዝብ ጥያቄን ይዘው ወደ ተለያዩ ተቋማት በማምራት እየጠየቁ መሆናቸውን የገለፁት ተወካዮቹ ዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ቅሬታ አሰምተዋል። ደራ የአማራ ማንነት ጥያቄ በማንሳቱና በቅርቡም ጥያቄው ወደ ማንነትና ወሰን ኮሚሽን መተላለፉን ተከትሎ ቅር የተሰኙ አንዳንድ አመራሮች የነፈጉት እድል ስለመሆኑ የገለፁት ሌላኛው ተወካይ ደራ በዞኑ ካሉት ወረዳዎች በመሬት ስፋት አንደኛ በመሆኑ ለግንባታ የቦታ ችግር የለበትም ብለዋል። በመሆኑም የራሳቸው የአመራሮቹ ፍላጎትና ፈቃደኝነት አለመኖር ካልሆነ በስተቀር ከግንባታ መሬት ጋር በተያያዘ የሚነሳ ችግር የለም ባይ ናቸው። ፕሮጀክቱ ታጥፏል እስከፈለጋችሁበት መሄድ ትችላላችሁ የሚል ምላሽ በዞን መሰጠቱን ተከትሎም እስከ አዲስ አበባ ድረስ በመምጣት የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ገብተው ለማናገር እንደሞከሩ ገልፀው ነገር ግን የዞኑ ጉዳይ ነው ከማለት ባለፈ ፈቅደው እንኳ በጎ ምላሽ አልሰጡንም ብለዋል። በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ቅሬታ ሰሚ በማቅናትም እድላችን ለምን ይታጠፋል በሚል ድምጻቸውን አሰምተዋል። የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ቅሬታ ሰሚውም በኦሮሚያ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር እና የክልሉ ትምህርት ጽ/ቤት ምክትልን በቀጥታ በስልክ ያነጋገራቸው ሲሆን በመካከላቸው አለመግባባት እንደነበር ታዝበናል ብለዋል ቅሬታ አቅራቢዎቹ። ማህበረሰቡም ካሳ እንደማይጠይቅና የቦታ ችግር እንደሌለባቸው የገለፁት ተወካይ በቅርቡ 16.04 ሄክታር ለግንባታ የሚሆን መሬትን ቃለ ጉባኤ በመያዝ ፈርመው ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ቅሬታ ሰሚ ማስገባታቸውና ት/ቤቱ ሊነሳባቸው እንዳይገባ መጠየቃቸውን አስታውቀዋል። የሀይማኖት አባቶችና ሌሎች ማህበረሰቡን የወከሉ ተወካዮች የተሳተፉበት ሲሆን ያነሱትን ቅሬታም ጽ/ቤቱ መርምሮ ምላሽ እንደሚሰጥበት ተገልጧል። እንደ ኦሮሚያ ክልል ከተያዙት ፕሮጀክቶች መካከል 3 እንደተሰጣቸው የገለፁት የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ በበኩላቸው የተፈቀደም ሆነ የተነሳ ፕሮጀክት የለም ሲሉ አስተባብለዋል። ለሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤት ግን በቂ የመሬት ዝግጅት ባላቸውና የትምህርት ቤት እጥረት ያለባቸውን ወረዳዎችን በመለየት በዞኑ የተሰጠ እድል እንጅ ለእገሌ ወረዳ ተብሎ ከላይ ተወስኖ የመጣ ፕሮጀክት አይደለም ብለዋል። ለሰሜን ሸዋ ዞን ከክልል እድሉ ከተሰጠ በኋላ ራሱን የቻለ ኮሚቴ በማቋቋም በቦታው ላይ ተገኝቶ ሳይት ፕላንን በማጥናት ስታንዳርዱን ማሟላቱ ለተረጋገጠላቸው ወረዳዎች የተሰጠ ነው ያሉት አቶ ፀጋዬ 12 ሄክታር መሬት የሚፈልግ ፕሮጀክት መሆኑንም ጠቅሰዋል። የተለያዩ ባለሙያዎች ወርደው ሲለኩ እና የሳይት ጥናት ሲያደርጉ በመመልከት ብቻ በማህበረሰቡ ዘንድ እንደተሰጠ ታስቦ ሊሆን ይችላል እንጅ ኦፊሻል የተሰጠም የተነሳም ፕሮጀክት የለም ነው ያሉት። አቶ ፀጋዬ ሲቀጥሉ እንደ ትምህርት አመራር ወደ ደራ ወረዳ በማምራት ከአመራሩ እና ከህዝቡ ጋር ከ3 ጊዜ በላይ በመነጋገር እውነታውን እንዳሳዩ፣ከዞን አመራሮች ጋርም መወያየታቸውን ጠቁመዋል። በቦታው ላይ ወረዳው በቂ የመሬት ዝግጅት አልነበረውም ያሉት አቶ ፀጋዬ ፕሬጀክቱ ካሳ የማይከፈልበት በመሆኑ ባለመሬቶችንና የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግረን የቀረ ነው ብለዋል። ስራው የሚጀመረው በቅርብ ቀናት በመሆኑና ሰብላቸው ገና ባለመሰብሰቡ፤ አርሶ አደሮችም ሌላ የኢኮኖሚ አማራጭ እንደሌላቸው በመግለጻቸው ወረዳው በሌላ ጊዜ በሚገኝ እድል ተጠቃሚ ይሆናል በሚል ስለመወሰኑ ተናግረዋል። የሚመለከታቸውን ሌሎች የመንግስት አካላትን አድራሻ እንዳገኘን ፈቅደው ምላሽ ከሰጡን አካተን የምንመለስ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply