
በሸዋ አጣዬ እና አካባቢው ጀውሃ፣ሸዋሮቢት እንዲሁም አካባቢው በአማራ ልዩ ሀይል ላይ የተፈጸመው ጥቃት ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን የአማራ ወጣቶች ማህበር በደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ ገለጸ፤ ለአማራ ልዩ ኃይል አባላት ያለውን አብሮነትም ገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ልዩ ሀይል ፣የአማራ ፋኖ እና ሚኒሻ የአማራ ወጣቶች ማህበር በደብረብረሃን ቅርንጫፍ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታውቋል። የአማራ ወጣቶች ማህበር የደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ በአጣዬ እና አካባቢው ለሚገኙ የወገን ሀይሎች ከ60 ደርዘን በላይ የሚጠጣ ውሃ ድጋፍ አድርጓል። በአማራ ክልል በሸዋ አጣዬ እና አካባቢው ጀውሃ፣ሸዋሮቢት እንዲሁም አካባቢው በአማራ ልዩ ሀይል ላይ ሆን ተብሎ በተቀነባበረ መልኩ ጥቃት መድረሱና መፈፀሙ የሚታወስ ነው። የአማራ ወጣቶች ማህበርም በደረሰው የወገናችን ሀይል ጉዳት ፣ ክህደት ቁጭት ቢሰማውም ፤የአማራ ልዩ ሀይል የደረሰውን ክህደት ለመቀልበስ እና የኦነግ ተላላኪዎችን አስተምሮ ቅጣት ቀጥቶ ለመመለስ በውጊያ ለቆዩ ወንድሞቻችን:_ ከዚህ መካከል ለወገን ጦር ከ60 ደርዘን በላይ የሚጠጣ ውሃ ማቅረብ አንዱ ተግባር ነበር። በቀጣይም የአማራ ወጣቶች ማህበር በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ከጀግናው የአማራ ልዩ ሀይል ፣የአማራ ፋኖ እና የአማራ ሚሊሻ ጎን መሆናችንን እየገለፅን ለሁለተኛ ዙር አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናችንን መግለፅ እንወዳለን።
Source: Link to the Post