በሸዋ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የአማራ ወጣት እና የአብን አደረጃጀቶች በተለያዩ ወረዳዎች የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው ቀጥለዋል። አማራ ሚዲያ…

በሸዋ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የአማራ ወጣት እና የአብን አደረጃጀቶች በተለያዩ ወረዳዎች የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው ቀጥለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር በነጭ ጤፍ አምራችነቱ በሚታወቀው ምንጃር የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል እና ቀድመው የደረሱ ሰብሎችንም ለመሰብሰብ በሚል የተደራጁ ወጣቶችን ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ስፍራው ማሰማራቱን አስታውቋል። ትላንት እሁድ ከመርሃቤቴ በመነሳት ወደ ምንጃር ያቀናው የመርሃቤቴ_ምንጃር ዘማች ቡድን ደብረብርሃን ላይ ሲጠብቀው ከነበረው የደብረብርሃን_ምንጃር ዘማች ሸዋ አማራ ወጣት ማህበር አባላት ጋር በመጣመር ነው በማለዳ የምንጃር ጉዞውን ማድረጉን ያስታወቀው። የታታሪውን፣ የደጉን እና ጀግናውን የምንጃር ገበሬ ወገናችንን በመደገፍ ከጎኑ መሆናችንን ለማሳየት በሚል የተደረገ ዘመቻ ስለመሆኑ ነው ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው። በተመሳሳይ የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋም በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሳወቀው በሌሊት ወደ ምንጀር ተጉዞ የአርሶ አደሩን ሰብል በመሰብሰብ ላይ ይገኛል። ሌሎች በየቦታው ያሉ የወጣት ማህበራት አንበጣ በተከሰተበት አካባቢዎች በማቅናት የአርሶ አደሩን ሰብል ከበርሃ የአንበጣ መንጋ አፍ እንድትታደጉት ስንል ለሚመለከተው ሁሉ ጥሪያችን እናስተላልፋለን ብሏል። የችግሩን አሳሳቢነት የተመለከተው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄም (አብን) መንግስትን በመግለጫ ከማሳሰብ አልፎ ለመዋቅሩ፣ለተለያዩ አደረጃጀቶችና ለመላው አማራ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም እንደአብነት ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም የሸዋሮቢትና ቀወት ወረዳ አብን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ ከሰሜን ሸዋ ዞን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ፣ ከሀገረ ማርያም ከሰም ወረዳ የአብን አመራሮች ፣ ከደ/ብርሀን አብን ጽ/ቤት አመራሮች ፣ ከአባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ከአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ጋር በመተባበር ለአንበጣ መንጋ ስጋት በሆኑ አካባቢዎች በማቅናት የደረሰ የአቅመ ደካማ ወገኖችን ሰብል በመሰብሰብ በድጋሜ አጋርነቱን ማሳየቱን መግለፁ ይታወሳል። በተደረገው የድጋፍ ተሳትፎም ከ65 ሰው በላይ የሰው ሀይል በማሳተፍ 4 ጥማድ ገደማ የሚሆን የጤፍ ማሳ የታጨደ ሲሆን በቀጣይም አስፈላጊ በሆነው ድጋፍ ሁሉ ከአርሶ አደሩ ጎን እንደማይለዩ አስታውቀዋል። በሸዋ የአሳግርት ወረዳ ማህበረሰብም ወደ ምንጃር አቅንቶ አዝመራው በአንበጣ መንጋ ከመወረር እንዲድን የደረሱ ሰብሎችን እየሰበሰበ ይገኛል። የበረሃ አንበጣ መከላከል ስራው በመ/ብላ፣በአክርሚት እና በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ እልህ አስጨራሽ ሆኖ ስለመቀጠሉ፣ ሰራተኛውና አመራሩ ተቀናጅቶ እየታገለ መሆኑና ከሀገረ ማርያም ወረዳም ድጋፍ እንዳልተለው የተገለፀ ቢሆንም በሰ/ሸዋ ዞን በረኸት ወረዳ ምንታምር ቀበሌ የገባው የበረሃ አንበጣ የተዱ ንዑስ ቀበሌን ሰብል ሙሉ በሙሉ ጨርሶ ወደ ዳንሴ እና ጎሜንሣ ንዑስ ቀበሌዎች ገብቶ ጉዳት እያደረሰ ነው ተብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply