በሸዋ የደራ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የመ/ር ሀይለ ሚካኤል አርዓያ ታላቅ ወንድም አቶ ዋሲል አርዓያ ባልታወቁ አካላት ተገድለው ስለመገኘታቸው ነዋሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲ…

በሸዋ የደራ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የመ/ር ሀይለ ሚካኤል አርዓያ ታላቅ ወንድም አቶ ዋሲል አርዓያ ባልታወቁ አካላት ተገድለው ስለመገኘታቸው ነዋሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሸዋ የደራ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ የመ/ር ሀይለ ሚካኤል አርዓያ ታላቅ ወንድም አቶ ዋሲል አርዓያ በደራ ወረዳ ጉንዶ መስቀል ከተማ ልዩ ስሙ ኬራ ኪዳነ ምህረት ፀበል አካባቢ ባልታወቁ አካላት ተገድለው ስለመገኘታቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል። አቶ ዋሲል አርዓያ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ በገደል ተጥለውና ህይወታቸውም አልፎ ስለመገኘታቸው ከጉንዶ መስቀል የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አቶ ዋሲል ባለትዳርና የልጆች አባት ስለመሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በማንና እንዴት እንደተገደሉ ግን ገና በፖሊስ እየተጣራ ስለመሆኑ ነው ምንጮች የተናገሩት። የመረጃ ምንጫችን ሲቀጥሉ ግድያው ምንም እንኳ ገና የሚጣራ ቢሆንም ሆነተብሎ በሸዋ የደራ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን ከፍተኛ ትግል እያደረጉ ያሉትን መ/ር ሀይለ ሚካኤል አርዓያን ከትግል ለማስቆም፣ለመጉዳት ወይም ለመበቀል ሲባል ደካማና እኩይ አስተሳሰብ ባላቸው ፅንፈኛ ኦነጎች ተፈፅሞ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል። መ/ር ሀይለ ሚካኤል በሸዋ የደራ አማራ ላይ የሚፈፀመው ተደራራቢ ግድያ፣መፈናቀልና ዝርፊያ እንዲቆም፣ የአማራዎች መብት፣ጥቅምና ፍላጎት እንዲከበርላቸው፣ የማንነትና የእርስት ጉዳይም በህጋዊ መልኩ በፌደሬሽን ም/ቤት ውሳኔ እንዲሰጠው እየታገሉ መሆናቸው ይታወቃል። መ/ር ሀይለ ሚካኤል የአማራ ሚዲያ ማዕከልን ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም በህዝብ ላይ የሚደርሰው ተደጋጋሚ ግፍና በደል አንዳች መፍትሄ ይሰጠው ዘንድ ያለመሰልቸት ድምፅ በመሆንም ይታወቃሉ። መ/ር ሀይለ ሚካኤል ሚያደርጉት ትግል በደራ ወረዳ መስተዳድር አካላት ባለመወደዱና ይህን ተከትሎም በደረሰባቸው ከፍተኛ እስርና እንግልት ከአካባቢው ለመልቀቅ መገደዳቸው ይታወሳል። ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን አካተን የምንመለስ ይሆናል። ነፍስ ይማር! መፅናናትን ተመኘን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply