You are currently viewing በሸዋ ደራና ግራር ጃርሶ በኦነግ ሸኔ የአማራ ተወላጆች እየተገደሉ  መሆኑ ተገለፀ።  ታህሳስ 24/2014/አሻራ ሚዲያ /  በግራር ጃርሶና በሌሎች የሸዋ ከተሞች አምቦ አቅራቢያን ጨምሮ ኦነግ…

በሸዋ ደራና ግራር ጃርሶ በኦነግ ሸኔ የአማራ ተወላጆች እየተገደሉ መሆኑ ተገለፀ። ታህሳስ 24/2014/አሻራ ሚዲያ / በግራር ጃርሶና በሌሎች የሸዋ ከተሞች አምቦ አቅራቢያን ጨምሮ ኦነግ…

በሸዋ ደራና ግራር ጃርሶ በኦነግ ሸኔ የአማራ ተወላጆች እየተገደሉ መሆኑ ተገለፀ። ታህሳስ 24/2014/አሻራ ሚዲያ / በግራር ጃርሶና በሌሎች የሸዋ ከተሞች አምቦ አቅራቢያን ጨምሮ ኦነግ ሸኔ ከፍተኛ ወንጀል እየፈጸመ በመንግስት ባለስልጣናት ዝም ተብሏል። ከደራና ጉንደመስቀል ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል መሳሪያዎቹን በመጋዘን አስቀምጦ ተሽከርካሪ ፒካፕ መኪናዎቻቸውን እየተዉ ወደ ናዝሪት አዳማና ቢሾፍቱ ደብረዘይት ካምፖች እየሄዱ መሆኑ ታውቋል። በምትካቸው የኦነግ ሸኔ ኃይሎች በደራ እና አከባቢው ገብተው መሳሪያዎችን በመውረስና መኪኖችን በመውሰድ ንጹሃንን እየገደሉ መሆኑ ተሰምቷል ። በሸዋ ደራ በርካታ ሰዎችን በኦነግ ሸኔ ሞተዋል ከሶስት ቀበሌ በላይ የገበሬው ሰብል ተቃጥሏል። የደራን ዋና ከተማ ጉንደ መስቀልን ለመያዝ 5 ኪሎ ሜትር ላይ ትልቅ ተጋድሎ እየተደረገ ይገኛል። የወረዳውም አስተዳደርም ከአቅማችን በላይ ነው ያለ ሲሆን የኦነግ ሃይል በሶስት አቅጣጫ በመትረዬስ፣ በስናይበር ከላሽ ከያዘ የደራን ገበሬ ገጥሞታል የኦሮሚያ ልዩ ሃይልም የወረዳውን አመራር በመክዳት እየሸሸ ይገኛል ተብሏል ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply