በሸዋ ደራ ጀማ ወንዝ አካባቢ የኦነግ ሸኔ አባላት ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጀ እንደሆነ ተሰማ።   አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ        ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም…

በሸዋ ደራ ጀማ ወንዝ አካባቢ የኦነግ ሸኔ አባላት ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጀ እንደሆነ ተሰማ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም…

በሸዋ ደራ ጀማ ወንዝ አካባቢ የኦነግ ሸኔ አባላት ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጀ እንደሆነ ተሰማ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከ400 በላይ የኦነግ ታጣቂዎች ጀማ ወንዝ መቲ ቀበሌ ላይ ሰፍሮ እንደሚገኝ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ገልፀዋል። በደራ ደጀንና ሸበል በረንታ በርሀማ ቦታዎች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እየተዘጋጀ እንደሆነም ተገልጧል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደራ እና አካባቢው የገበሬውን ህጋዊ መሳሪያቸውን እንዲያወርዱ እየተገደዱ እንደሆነም ተናግረዋል። የኦነግ ታጣቂዎች ከነሀሴ ወር 2012 ዓም ጀምሮ በቦታው የሰፈሩ ሲሆን አካባቢውን በተለያየ ጊዜ እተዘዋወሩ እያጠኑት ስለመሆናቸውም ገልጸዋል፡፡ የአባይና የጀማ ወንዝ ሸለቃማ ቦታዎች ለመመሸግ ምቹ በመሆናቸው ለወራት ቦታው ላይ አድፍጠው እንደሚገኙ ነው የአካባቢው ነዋሪዎች የገለጹት፡፡ ከአሁን በፊት በደራ እና አካባቢው ነዋሪዎች በተለያየ በግብርና ስራ ላይ በነበሩበት ሰዓት እነዚህ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ሲገድሉ እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን ቁጥራቸው እየበዛ በመምጣቱ ያልተጠበቀ ጥቃት ሳይፈጽሙብን የመንግስት የፀጥታ ሀይል ተገቢውን እርምጃ ይውሰድልን የሚል ሀሳብ ሰንዝረው እንደነበር አሻራ ሚዲያ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ህጋዊ መሳሪያችንን አናወርድም ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎችም አካባቢያቸውን ለቀው የአባይ ሸለቋማ ቦታዎችን ተሻግረው ወደ ጎጃም ሸበል በረንታ እና ደጀን እየሸሹ እንደሆነ ገልፀውልናል። በተመሳሳይ ዜና በትናንትናው እለት በቡሬ ከተማ ከ7 በላይ የኦነግ ታጣቂዎች መያዛቸው ይታወቃል። አሻራ ሚዲያ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply