You are currently viewing በሸዋ ደራ ጉንዶ መስቀልንና አካባቢውን ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከፍተኛ እልቂትና ወረራ የታደጉ የአማራ ሚሊሾችና አርሶ አደሮች በመንግስት እየተሳደዱ መሆኑን አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

በሸዋ ደራ ጉንዶ መስቀልንና አካባቢውን ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከፍተኛ እልቂትና ወረራ የታደጉ የአማራ ሚሊሾችና አርሶ አደሮች በመንግስት እየተሳደዱ መሆኑን አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

በሸዋ ደራ ጉንዶ መስቀልንና አካባቢውን ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከፍተኛ እልቂትና ወረራ የታደጉ የአማራ ሚሊሾችና አርሶ አደሮች በመንግስት እየተሳደዱ መሆኑን አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በሸዋ ደራ ጉንዶ መስቀልንና አካባቢውን ከከፍተኛ እልቂትና ወረራ የታደጉ የአማራ ሚሊሾችና አርሶ አደሮች በመንግስት እየተሳደዱ መሆኑን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) አስታውቀዋል። በየጫካው እየተሳደድን ነው የሚሉት በደራ የሚኖሩ የአማራ ሚሊሾች እና አርሶ አደሮች ቁጥራቸው ከ115 በላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና ም/አስተዳዳሪ የኦሮሞ ተወላጆች ቢሆኑም ኦነግ ሸኔ በጉንዶ መስቀል ከፈጸመው ጥቃት መቀልበስ ጋር ተያይዞ በአካባቢው ሚሊሾችና አርሶ አደሮች በተሰጠው የአጸፋ ምላሽ ቅር በተሰኙ የዞን እና የክልል አመራሮች ወዲያውኑ ከስራ ተባረዋል ተብሏል። በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች እንደለመደው ባሰበው ልክ በጉንዶ መስቀል ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እና የባንኮች ዝርፊያ መፈጸም ሳይሳካለት በመቅረቱ በውስጥም ሆነ በጫካ ያሉ የሽብር ቡድኑ አማራን የማጥፋት ክፉ አላማ ተጋሪዎች አካላት መበሳጨታቸው ተገልጧል። በዚህም ምክንያት የሽብር ቡድኑ አባላት ከጉንዶ መስቀል ሲመለሱ በቆሮ ገንደ በርበሬ እና በአደጫ አካባቢ ከፍተኛ ግድያ፣ እገታ እና ዝርፊያ ፈጽመዋል። ከተማዋን ከወራሪው ጥቃት የታደጉ የጉንዶ መስቀል፣ የቱቲ እና የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ከ115 በላይ የአማራ ሚሊሾችንና አርሶ አደሮችን “ፖሊስ ጣቢያ ልትዘርፉ ነበር” የሚል አሳፋሪ እና አስቂኝ ውሸት በማቀነባበር ተወንጅለው በኮማንድ ፖስት እየተሳደዱ መሆናቸው ተገልጧል። ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እየፈጸመ ባለው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ላይ እርምጃ በመውሰድ ንጹሃን ታጋቾችን ለማስለቀቅ የሚያስችል እርምጃ ለመውሰድ ያቀኑ ሚሊሾችም በመንግስት ክልከላ ተደርጎባቸዋል። በመንግስት እየተሳደዱ ያሉ እነዚህ አካላት በእርግጥም መሳደድ ሳይሆን ሽልማት ይገባቸው እንደነበር ገልጸዋል። አስተያየት ሰጭዎቹ ህዝባችንን ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እንዳንከላከልም ስንጨፈጨፍ ያልደረሰውን መከላከያ ሰራዊት በማዘዝ ወደ ቡድኑ መሄጃ መስመር ላይ በማስፈር ለሸኔ ያላቸውን ውግንና በግልጽ አሳይተዋል ባይ ናቸው። በመጨረሻም የፌደራል መንግስት በአስቸኳይ ጉዳዩን በትኩረት ተመልክቶ መፍትሄ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply