የትግራይ መንግሥት ምሥረታ በተጨባጭ በሕግ…….. (De facto state of Tigray 24 May 1991)
በትግራይ ሕግወጥ መንግሥት ምሥረታ …………..…….. (Dejure state of Tigray 2018)
የትግራይ መንግሥት ምሥረታ በተጨባጭ በሕግ ከግንቦት 1983 ዓ/ም ጀምሮ የትግራይ ክልል ብሄራዊ መንግሥት ተብሎ ተቆቆመ፡፡ ህወሓት ከሻብያ ጋር በበድማ ጦርነት በቀሰቀሰ ጊዜ የሃገሪቱ መከላከያ ሠራዊት የአየር ኃይል ተዋጊ ጀቶች፣ ታንከኛ ብርጌድ፣ እግረኛ ጦር ሠራዊት፣ ጠቅላይ የጦር ግምጃ ቤቱ ሁሉንም በመውስድ የትግራይ መንግሥት በመቐለ በሕግወጥ መንገድ መሽጎ ተመሠረተ፣ ሽብር ስፖንሰር እያደረገ የጦር መሣሪያና ገንዘብ በማስታጠቅ ሽብር በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም የተነሳ በመላ ሃገሪቱ ውስጥ ከ2.5 እስከ 3 ሚሊዮን ህዝብ መፈናቀል፣ ኢኮኖሚው እንዳያንሰራራና የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዳያድግ እንዲሁም የምግብ ፍጆታ የዋጋ ግሸበት መጨመር፣ የቤንዚል እጥረት መከሰት አስከትሎል፡፡ የ10 ቢሊዮን ብር የግብርና ታክስ አለመሰብሰብ በአጠቃላይ ወያኔ የኢኮኖሚ አሻጥር በየፈርጅ በማከናወን ላይ እንዳለ መረዳት ያሻል፡፡ ሆኖመረ ኤች አር 128 ኢትዮጵያ ውስጥ ስብአዊ መብት መደገፍና ሁሉን አቀፍ የሆነ አስተዳደደር ለማበረታታት የወጣው የህግ ረቂቅ የዶክተር አብይን መንግሥት ለማገዝ የማግኒስኪ እርምጃ በቀድሞው የደህነት ኃላፊ ጌታቸው አሰፋ እንቅስቃሴና ሃብት ለማገድ እንቅስቃሴ ጀምሮል፡፡ መቐለ ለመሸገው ጸረ ዴሞክራሲ ኃይል ትልቅ ማስጠንቀቂያ በመሆኑ የዲያፖራው ወገናችን ድምፃችሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ ማሰማትና ያለ ትግል ነፃነት እንደማይገኝ በመገንዘብ እውነቱን መጋፈጥ ይኖርባችሆል፡፡ በመንግሥት ውስጥ መንግሥት የአዲስ አበባና የመቐለ የፖለቲካ የኃይል ሚዛን ጉተታ የሰው ህይወት እየረገፈ ይገኛል፣ በሃገሪቱ የህግ ሉዓላዊነት የለም፡፡ በሹምባሹ የወያኔ መንግሥት ላይ የተቀናጀ የኢኮኖሚ ማቅቀብ በማድረግ የወያኔ ልዩ ኃይልን ትጥቅ እስኪፈታና የህዝብ ልጆች ግድያ እስኪያቆም ትግሉ መቀጠል አለበት እንላለን፡፡ የፈራ ይመለስ! ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ!!!
{1} የትግራይ ክልል ድንበርና ወሰን ከጎንድር (ወልቃይት)፣ ከወሎ (አላማጣ፣ ቆቦ፣) እና ከአፋር መሬት በመውሰድ የተቆቆመ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት በትግራይ ልዩ ኃይል ጦርነት ከፍቶ የህዝብ ልጆች በመግደል ላይ ይገኛል፡፡ ከመቐሌ መሸገው ማፍያ በመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኖች ከአዲስ አበባ እያስጠሩ ማናፋት ጀምረዋል፣ አንዴ አባይ ፀሃዬ አንዴ የሜቴኩ ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ስማችን ጠፋ እያሉ ክስ ጀምረዋል፡፡ እስከመቼ እህ ህ እስከመቼ እህ ህ!!!
{2} በሃረሪ ክልላዊ መንግሥት በሀብሊና ኦህዴድ የግፍ አገዛዝ ሃረርና የድሬዳዋ ህዝብ የአዲሱ የዴሞክራሲያዊ ለውጥ ተቆዳሽ መሆን አልቻለም፡፡
{3} የአዲስ አበባ ወጣቶች ዴሞክራሲያዊ ትግል በተካሄደ ሠላማዊ ሠልፍ በግፍ 5 ወጣቶች ሞተዋል፣ በሽህ በላይ ወጣቶች ላይ ክስ ሳይመሰረተ በጦላይ እንዲታሰሩ መደረጉ ህዝባዊውን ትግል በፍርሃት ከቶታል፣ ወያኔ የገዳዬች በሪሞት የሚቆጣጠረው የገዳይ ኃይል እንዳለ ተረድተናል፡፡
{4} በአፍር ክልላዊ መንግስት የወያኔ ሽርካ የሆነውን መንግስት ለመገርሰስ በመታገል ላይ ይገኛል፣ ዱኮ ሂና (Duko-Hina) የአፋር ወጣቶች የህወሓት ኢፈርት የንግድ ድርጅት የሆኑትን የጨው ፋብሪካዎች ከአፋር በማስወጣት የዴሞክራሲያዊውን ትግል ተቀላቅሎል፡፡
{5} በጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ህዝባዊ ትግል በማድረግ የወያኔን ሴራ በመታገል ለዴሞክራሲያዊ ትግል በማቀጣጠል ላይ ይገኛል፡፡
{6} በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ህዝብ አዲሱን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባትና የወያኔን ሴራ በማጋለጥ ትግል አርጎል፡፡
{7} በሱማሌ ክልል መንግስት ህዝባዊ ትግል የህወሓትና የሶህዴፓ(አብዲ ኢሌ) የጦር አበጋዞች መንግሥት አሽቀንጥሮ በመጣል የዴሞክራሲያዊውን ትግል ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አድርጎል፡፡ በተመሳሳይ የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ (2008-2012)፣ ውድቅ ሆኖ ሌላ ተለወጭ እቅድ መነደፍ አለበት እንላለን፡-
- በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ከግብርና ምርቶች የውጪ ንግድ 7.7 ቢሊዩን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶል ይል ነበር ከሽፎል፡፡
- በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ከኢንዱስትሪ ምርቶች የውጪ ንግድ 4.6 ቢሊዩን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶል ይል ነበር ከሽፎል፡፡
- በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ከኤሌትሪክ ኃይል ኤክስፖርት (የውጪ ንግድ) 636 ሚሊዩን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶል ይል ነበር ከሽፎል፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ በአግባቡ አለመጀመር ለሌላ የኢኮኖሚ ኪሣራ ሃገሪቱን ይዳርጋል እንላለን፡፡
- በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ከማእድን ዘርፍ ኤክስፖርት (የውጪ ንግድ) 2.1 ቢሊዩን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶል ይል ነበር ከሽፎል፡፡ የለገደንቢው የሸክ አላሙዲን ሜድሮክ ጎልድ በህብረተሰቡ ተቃውሞ ቀርቦበት ከሥራ ውጭ በመሆኑ የውጭ ምንዛሪ አሽቆልቁሎል፡፡ ኢዛና የወርቅ መዕድን በህወሓት ንብረትነት የውጭ ምንዛሪ እየዘረፉ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የአላሙዲንና የወያኔን የተመረተ የወርቅ ማዕድን ብሄራዊ ባንክ ሳይገባና ሳይመዘገብ በቀጥታ ወደ ውጭ ሃገር እንደሚሄድ የባንኩ ኃላፊዎች ተጠያቂ ሳይሆኑ፣ የባሌስ ለሌላ ሹመት ታጭተዋል፡፡ ከባንክ ፋይናንሻል ዘርፍ ውስጥ ሙስናና ሌብነት ሠንሠለት ድር ባለመበጣጠሱ አዲሱ ለውጥ አደጋ ውስጥ ነው፡፡ የውጭ ምንዛሪ ተጠቃሚዎቹ አሁንም የወያኔ/ኢህአዴግ የፖለቲካ የንግድ ድርጅቶች ባንኮች፣ የኢንፖረተሮች ናቸው፡፡
- በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ከጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ የውጪ ንግድ 1 ቢሊዩን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶል ይል ነበር ከሽፎል፡፡
- በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ከቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የውጪ ንግድ 800 ሚሊዩን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶል ይል ነበር ከሽፎል፡፡ በአንደኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከዘርፉ 508 ሚሊዩን ዶላር ገቢ ተገኝቶ ነበር፡፡
- በአጠቃላይ የውጪ ንግድ ከጠቅላላው የሃገር ውስጥ ምርት የሚኖረው ድርሻ 11.8 በመቶ ድርሻ እንዲኖረው ውጥን ተይዞል ይል ነበር ከሽፎል፡፡ የውጭ ንግድ ገቢ እቅድ በ2007 ዓ/ም (3,019.3 ቢሊዩን ዶላር)፣ በ2008 ዓ/ም (4,884.6 ቢሊዩን ዶላር)፣ በ2009 ዓ/ም (6,780.3 ቢሊዩን ዶላር)፣ በ2010 ዓ/ም (8,747.8 ቢሊዩን ዶላር)፣ በ2011 ዓ/ም (11,035.6 ቢሊዩን ዶላር)፣ በ2012 ዓ/ም (13,909.1 ቢሊዩን ዶላር) ለማግኘት ታቅዶል ይል ነበር ከሽፎል፡፡ የውጭ ንግድ ገቢ እቅድ ከ2008 እስከ 2009 ዓ/ም የእቅዱ አፈፃፀም 3 ቢሊዩን
- የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በሆለተኛረ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ 5779 ኪሎሜትር መንገድ 4579 ኪሎሜትር አድሳትና ግንባታ አካሂዶል፡፡ በክልሎች ተፈፃሚ የሚሆነው ሁሉን አቀፍ የገጠር መንገዶች ልማት ፕሮግራም እስከ 90 ሽህ ኪሎ ሜትር መንገድ ለመገንባት ታቅዶ አፈጻፀሙ ከአስር በመቶ እንዳልበለጠ ዳሬክተሩ አቶ ሳምሶን ወንድሙ ገልፀዋል፡፡ ብሁ ህዝብ በክልሎች እየተፈናቀለ ሥራው ሊሰራ አልቻለም፣ የግብርና እርሻ ልማቱ ተስተጎጉሎል፣ የተፈናቃይ ወገኞችን ለመንከባከብ ተጨማሪ በጀት ይጠይቃል፡፡
የህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን /ኢህአዴግ ፖለቲካኛ ካድሬዎች የልማታዊ መንግሥት ቃልቻ ድቤ መቺዎችና አብዬታዊ ዴሞክራሲ ቱልቱላዎች ምንም አዲስ ለውጥ አያመጡም እንላለን፡፡ ህወሓት/ ኢህአዴግ ወደ ኦህዴድ/ኢህአዴግ ለውጥ በማድረግ ምንም የፖለቲካና ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ ሳይቀርፅ አዲስ ለውጥ አይመጣም፡፡ መቐለ የመሸገው የህወሓት ቡድን አይን ያወጣ ዝርፍያ ማንም ተጠያቂ እንደማይሆኑና ከህግ በላይ ያሉ የቀድሞ ሹመኞች በህግ ፊት እንደማይቀርቡ በመንግሥት ውስጥ መንግሥት የነበረው ህወሓት መንግሥት ትግራይን ከኢትዮጵያ መገንጠሉ የትግራይ ልዩ ኃይል በአማራና አፋር ክልል ጥቃት ሲሰነዝር የኢትዮጵያ መንግሥት ማስቆም አለማስቻሉ አስገራሚ ሆኖል፡፡ (De facto state of Tigry 24 May 1991) በትግራይ ሕግወጥ መንግሥት ምሥረታ (Dejure state of Tigry 2018 ) ተሸጋግሮል፡፡ ወያኔ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ በማደከምና አሻጥር በመፍጠር የተጀመረውን ለውጥ አደጋ ውስጥ በመክተት ላይ ይገኛሉ፡፡ አሁንም የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ከውጭ ጥሬ ዕቃዎችን ማስገባት ስለማይቻል ኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ገና አላንሰራራም፡፡ በኤርትራና ኢትዮጵያ መንግሥት ህገ ወጥ የድንበር ንግድ የሃገሪቱን የውጭ ምንዛሪ የሚያሳጣ የንግድ ልውውጥ በህግና ሥርዓት እንዳይዝ በማድረግ ወያኔ የኢኮኖሚ አሻጥር በድንበር ንግድ ስበብ ቡና፣ ነዳጅ፣ ሰሊጥ፣ ጤፍ ወዘተ የመሳሰሉትን ሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ የምታገኝበትን ምርቶች ወያኔ ኢፈርት ድርጅቶች በመሸጥ የደለበ ትርፍ አግኝተዋል፡፡ የዶክተር አብይ መንግሥት በሁለቱ ሃገሮች ያለውን የንግድ ግንኙነት መልክ ማስያዝ የመንግሥት ኃላፊነት ነው እንላለን፡፡ የባንክ ፋይናንሻል ዘርፍ፣ የውጭ ምንዛሪ፣ የብድር አሰጣጥና አሰባሰብ እንዲሁም የተበላሸ ብድር ወዘተ ባለው የሙስናና ሌብነት ድርጅታዊ መረብ ላይ አፋጣኝ እርምት ያስፈልጋል፡፡ በወያኔ ኢኮኖሚ አሻጥር በተለይ ፎርጅድ የብር ኖት ዝውውር የኢኮኖሚው ውድቀት በማፋጠን፣ በባንክ ፋይናንሻል ዘርፎች ላይ የገንዘብ እጥረት፣ የዋጋ ግሽበት፣ የፍጆታ እቃዎች እጥረት፣ የኢንዱስትሪ ጥሬ እቃዎች እጥረት፣ ሥራ አጥነት፣ ይከሰታል እንላለን፡፡ የዶክተር አብይ መንግሥት የሃገሪቱን የ50 እና 100 የብር ኖት ሱዳን ውስጥ ማሳተም ትቶ፣ በአስቸኮይ በአውሮፓ ሃገራት በማሳተምና የብር ኖቶቹን መቀየር አሰፈላጊ ነው እንላለን፡፡
የህግ የበላይነት ይከበር!!! የወያኔ ገዳዬች ለፍርድ ይቅረቡ!!!
የወያኔ ልዩ ኃይል ትጥቅ ይፍታ!!! የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የጦር መሣሪያ ወደነበረበት ይመለስ!!!
በወያኔ ላይ የተጠናከረ ህዝባዊ እንቢተኛነትና ተጋድሎ በህብረት ተቀናጅቶ ይጠራ!!!
ነጻነት በትግል እንጂ በልመና አይገኝም!!! ደውሉ የሚደውለው ለነገ ሞቾች ነው!!!
በሹምባሹ የወያኔ መንግሥት ላይ፣ የተቀናጀ የኢኮኖሚ ማዕቀብ !!!