በሺኒሌ ወረዳ የጣለ ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ የአንድ እናትን ህይወት ሲያጠፋ በርካታ እንስሳትን መውሰዱ ተገለፀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም…

በሺኒሌ ወረዳ የጣለ ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ የአንድ እናትን ህይወት ሲያጠፋ በርካታ እንስሳትን መውሰዱ ተገለፀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም…

በሺኒሌ ወረዳ የጣለ ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ የአንድ እናትን ህይወት ሲያጠፋ በርካታ እንስሳትን መውሰዱ ተገለፀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን ሺኒሌ ወረዳ በጣለ ከባድ ዝናብ መርማርሳ የተባለው ወንዝ በመሙላቱ ያስከተለው የጎርፍ ማጥለቅለቅ የአንድ አርብቶ አደር እናትን ህይወት ሲነጥቅ ሲጠብቋቸው የነበሩ በርከት ያሉ ፍየሎችም በጎርፉ መወሰዳቸው ተገልጧል፡፡ የሺኒሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሁሴን አደም እንደገለጹት በወረዳው በጣለው ዝናብ ወንዙ ሞልቶ በደረሰው ጎርፍ ህይወታቸውን ያጡትን ግለሰብ አስከሬን የአከባቢው የፀጥታ አካላት የማፈላለግ ስራ እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ከባድ ጎርፍ በቅርቡ በአካባቢው ተወላጅ ዲያስፖራና በክልሉ ባለሃብቶች የተገነቡና ለማህበረሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ መሰረተ ልማት አውታሮችን ማፈራረሱንና ጉዳት ማድረሱንም ገልጸዋል። ሺኒሌ ከተማና ድሬዳዋን የሚያስተሳስረውን የአስፋልት መንገድም በጎርፉ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት መሆኑንም በመግለፅ የአካባቢው ህብረተሰብ በቀጣዩ ቀናት ሊጥል የሚችለው ዝናብን ተከትሎ ሊከሰቱ ከሚችሉ የጎርፍ አደጋዎች ጥንቃቄ እንዲያደርግና ከወንዝና ተፋሰስ አካባቢዎችም እንዲርቅ አሳስበዋል። ከቀናት በፊት በሽላቦ ወረዳ መብረቅ ቀላቅሎ የጣለ ከባድ ዝናብ የ160 ፍየሎችና የ4 ግመሎች ህይወት ማጥፋቱን አይዘነጋም። በወቅቱም የክልሉ አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ቢሮ በሚጥለው ዝናብ ምክንያት ተመሳሳይ አደጋ ሊገጥም እንደሚችል ገልጾ ህዝቡ አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰቡን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ምንጭ_የሶማሊ ክልል ፈጣን መረጃ

Source: Link to the Post

Leave a Reply