በሺዎች የሚቆጠሩ አፍጋኖች በየቀኑ ሃገራቸውን ለቀው እየተሰደዱ ነው

https://gdb.voanews.com/F6835BE4-80C8-4676-AD52-78F26CCBF728_w800_h450.jpg

ታሊባን ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ የአፍጋኒስታን ምጣኔ ሀብት እየወደቀ በመምጣቱ፣ ከአፍጋኒስታን እየተሰደዱ ወደ ኢራን የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ፡፡ 

ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ከ300ሺ ሰዎች በላይ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ወደ ኢራን መግባታቸው ተዘግቧል፡፡ 

የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት ይፋ እንዳደረገው መረጃ ከሆነ በየቀኑ ከ4 እስከ 5ሺ ሰዎች አፍጋኒስታንን እየለቀቁ ወደ ኢራን ይገባሉ፡፡ 

ምንም እንኳ የብዙዎቹ ፍላጎት ወደ አውሮፓ መሄድ ቢሆንም በኢራን የሚቀሩ ስለሆነ እስካሁን አውሮፓን የሚያሰጋ የስደተኛ ማዕበል ከአፍጋኒስታን አለመከሰቱም ተነግሯል፡፡ 

አንዳንድ ዘገባዎች ግን እንደሚያመለክቱት በቱርክ በኩል አድርገው ጣልያን ውስጥ የታዩት የአፍጋኒስታን ስደተኞች አሉ፡፡ 

ኢራን በየሳምንቱ ከ20 እስከ 30ሺ የሚሆኑ ስደተኞችን ወደ አፍጋኒስታን መልሳ ትልካለች፡፡ 

እስከለፈው ህዳር ወር ድረስ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን ወደ አፍጋኒስታን መልሳ ማበረሯ ተመልክቷል፡፡ 

ይሁን እንጂ አፍጋኖቹ በተባረሩ ቁጥር እየደጋገሙ ወደ ኢራን ተመልሰው ስለሚመጡ፣ ኢራን ውስጥ ያሉ የአፍጋን ስደተኞች ከ3 ሚሊዮን በላይ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply