
በሻሸመኔ ከተማ የሚገኘው የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት በመንግሥት የጸጥታ አካላት መታሸጉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 26 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በትናንትናው ዕለት የሀገረ ስብከቱ ዋና ፀሐፊና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው በድጋሚ መታሰራቸውን መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን ሌሎች የሀገረ ስብከት ሰራተኞችም እየተሳደዱ እንደሆነ ተገልጿል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ሕገ ወጡን ቡድን ተቀበሉ የሚል እንደሆነ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል (ተ.ሚ.ማ) ያጋራው መረጃ አመልክቷል።
Source: Link to the Post