
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ በተፈጠረ ውዝግብ ምክንያት የሰው ሕይወት መጥፋቱ እና የአካል ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። ከሁለት ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከሕግ ውጪ ነው ባለችው ሁኔታ ሹመት የተቀበሉት አባቶች ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ወዳሉ አብያተክርስቲያናት በሚያቀኑበት ጊዜ ነው በተፈጠረ ግጭት ጉዳት የደረሰው። በሰው ላይ የደረሰው ጉዳት መጠን በትክክል አልታወቀም።
Source: Link to the Post