በሽብር ተግባር ለተሰማራው የትሕነግ ቡድን በአንዳንድ አካባቢዎች ያልተገባ ጊዜ መስጠት በንፁሃን ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዲደርስ ስለሚያደረግ መንግስት አካሄዱን መፈተሽ ያስፈልገዋል ሲሉ አርበኛ…

በሽብር ተግባር ለተሰማራው የትሕነግ ቡድን በአንዳንድ አካባቢዎች ያልተገባ ጊዜ መስጠት በንፁሃን ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዲደርስ ስለሚያደረግ መንግስት አካሄዱን መፈተሽ ያስፈልገዋል ሲሉ አርበኛ…

በሽብር ተግባር ለተሰማራው የትሕነግ ቡድን በአንዳንድ አካባቢዎች ያልተገባ ጊዜ መስጠት በንፁሃን ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዲደርስ ስለሚያደረግ መንግስት አካሄዱን መፈተሽ ያስፈልገዋል ሲሉ አርበኛ ገበየሁ እንዬው አሳሰቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በጠለምትና አዳርቃይ ግንባር በኩል ከአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻው ጋር ተሰልፈው ትሕነግን የተፋለሙ፤ ምሽግ የደረመሱት እነ አርበኛ ገበየሁ እንዬው 10 የሚሆኑ መማረካቸውን አውስተዋል። በጠለምት እና አዳርቃይ መስመር በተለይም በዋልድባ አርማ ደጋ መስመር ተቆርጦ የቀሩና የተበተኑ የትሕነግ ጁንታዎችን በማሳደድ እየለቀምን እንገኛለን ብለዋል። የአሸባሪውን ትሕነግን ቡድን ያለ ማቆራረጥ ተከታትለን የመደምሰስና አካባቢውን ከአሸባሪው መረብ ማፅዳት ስራ አስፈላጊ ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል። የወልቃይት፣ጠገዴ፣ጠለምትና ራያ ህዝብም ለፀጥታ አካላት ቀድሞ መረጃ በመስጠት፣ነቅተው ራሳቸውንና አካባቢያቸውን በመጠበቅ የድርሻቸውን ማበርከት እንዳለባቸው ተናግረዋል። በትናንትናው እለት ዙ 23 የሚባሉ መሳሪያዎችን ጭምር ይዘው የሚንቀሳቀሱ ከከሃዲው ቡድን ታጣቂዎች ጋር በአርማ ደጋ መስመር የተኩስ ልውውጥ መደረጉን አውስተዋል። “መሳሪያ እንዴት አስረከብክ፤ ለምን ተማረክ” በሚል የትግራይ ሚሊሻዎችን የመደብደብና የማሰቃየት ወንጀል እየፈፀሙ ነው ያሉት አርበኛ ገበየሁ ለጁንታ ጊዜ መስጠት አያስፈልግም ሲሉ አክለዋል። በወልቃይት፣ጠገዴ፣በጠለምትና ራያ የአማራ ፋኖ ከልዩ ሀይሉ፣ከሚሊሻውና ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ተሰልፎ መስዋዕትነት በመክፈል የአማራ አፅመ እርስቶች ከቡድኑ ነጻ እንዲወጡ የድርሻውን እንደተወጣው ሁሉ የልማት ቀጠና በሆነውና በየቀኑ አማራ በጅምላ እየተገደለ ያለበት የመተከል ጉዳይም አሳሳቢ በመሆኑ መንግስት አፋጣኝ ውሳኔ በመወሰን የሀይል እርምጃ ሊወስድ ይገባል ነው ያሉት። እኛም እንደ አማራ ፋኖ በመተከል የሚያልቀውን ወገናችንን ለመታደግ በማንኛውም ጊዜ ዝግጁ መሆናችን ስንገልፅ መንግስት ፍቃድ እንዲሰጠን በመጠየቅ ጭምር ነው ብለዋል። ከአርበኛ ገበየሁ እንየው ጋር ያደረግነው ቃለ ምልልስን በአሚማ የዩቱብ አድራሻ የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply