በሽብር ተግባር የተሰማሩ የጉምዝ ታጣቂዎች ከዳንጉር ወደ ፓዌ ወረዳ በማቅናት ከብቶችን በመጠበቅ ላይ የነበሩ 2 አማራዎችን መግደላቸውና አንድ ብሬን መማረካቸው ተነገረ።    አማራ ሚዲያ ማዕ…

በሽብር ተግባር የተሰማሩ የጉምዝ ታጣቂዎች ከዳንጉር ወደ ፓዌ ወረዳ በማቅናት ከብቶችን በመጠበቅ ላይ የነበሩ 2 አማራዎችን መግደላቸውና አንድ ብሬን መማረካቸው ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕ…

በሽብር ተግባር የተሰማሩ የጉምዝ ታጣቂዎች ከዳንጉር ወደ ፓዌ ወረዳ በማቅናት ከብቶችን በመጠበቅ ላይ የነበሩ 2 አማራዎችን መግደላቸውና አንድ ብሬን መማረካቸው ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሽብር ተግባር የተሰማሩት የጉምዝ ታጣቂዎች ትናንት ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ከዳንጉር ጊቲ ቀበሌ ተነስተው ወደ ፓዌ ወረዳ ህዳሴ ቀበሌ በማቅናት ከብቶችን እየጠበቁ የነበሩ 2 እድሜያቸው የ15 እና የ16 ዓመት የሚሆኑ አማራዎችን በጥይት ተኩሰው ሲገድሉ አንደኛው እረኛ ሮጦ ማምለጡን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የተገደሉት ወጣቶችም ዛሬ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም በጓንጓ ወረዳ ዚገም ገብርኤል እና በፓዌ ወረዳ ህዳሴ ቀበሌ ስርዓተ ቀብራቸው መፈፀሙን ለማወቅ ተችሏል። በእለቱም ዘርፈው የወሰዷቸውን 150 የሚሆኑ ከብቶችን ለማስጣል የፓዌ ወረዳ ወረዳ የልዩ ሀይል አባላት፣ፖሊስና ሚሊሻዎች ተከታትለው ወደ ዳንጉር ወረዳ ጊቲ ቀበሌ አቅንተው ነበር። ይሁን እንጅ ወደ ጊቲ ቀበሌ ካቀኑት የፀጥታ አካላት መካከል 4 የልዩ ሀይል አባላትን ከአንድ ብሬን እና የጦር መሳሪያቻቸው ጋር ማርከው ያስቀሩ ስለመሆናቸው ተነግሯል። የተማረኩት የልዩ ሀይል አባላትም 3 የጉምዝ፣ አንድ የበርታ ብሄረሰብ ተወላጆች ሲሆኑ ልዩ ሀይሉ ብሬኑን ያስረከበው “ወደ እናንተ ነው የመጣነው እንዳትመቱን” ሲላቸው፤ “ወደ እኛ ከመጣችሁ መሳሪያችሁን ጣሉ” ሲሉት እንዳወረደላቸውና ሌሎች 3ቱም በተመሳሳይ መሳሪያቸውን እንዳስረከቡ ምንጮች ገልፀዋል። ከኋላ የነበሩ የፀጥታ አካላትም ወደ ኋላ በማፈግፈግ ሸሽተው ስለማምለጣቸው የነገሩን ነዋሪዎች የልዩ ሀይሉ አባል ሆነብሎ ብሬኑን እንዳስረከበ ነው የሚያምኑት። የፓዌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሀኑን ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡን በሚል ለማነጋገር ብንሞክርም ስብሰባ ላይ ነኝ በማለታቸው ለጊዜው ሀሳባቸውን ለማካተት አልተቻለም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply