You are currently viewing በሽብር ወንጀል ከሰነዋል በሚል የደቡብ ጎንደር ዞን ከደብረ ታቦር ማ/ቤት የተረከበው የአብን የዞን ስራ አስፈጻሚ ቢሰጥ አሰፋ በ20 ሽህ ብር ዋስትና ተፈቷል።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በሽብር ወንጀል ከሰነዋል በሚል የደቡብ ጎንደር ዞን ከደብረ ታቦር ማ/ቤት የተረከበው የአብን የዞን ስራ አስፈጻሚ ቢሰጥ አሰፋ በ20 ሽህ ብር ዋስትና ተፈቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በሽብር ወንጀል ከሰነዋል በሚል የደቡብ ጎንደር ዞን ከደብረ ታቦር ማ/ቤት የተረከበው የአብን የዞን ስራ አስፈጻሚ ቢሰጥ አሰፋ በ20 ሽህ ብር ዋስትና ተፈቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የስራ አስፈጻሚ አባል የሆነው አቶ ቢሰጥ አሰፋ በደብረ ታቦር ፖሊስ ጥቅምት 2/2015 ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ መታሰሩን አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) መዘገቡ ይታወሳል። በደብረ ታቦር ከመኖሪያ ቤቱ እያለ ድንገተኛ የአፈና እስር የተፈጸመበት ቢሰጥ አሰፋ መጀመሪያ ላይ ጥቅምት 1/2015 ከተሰጠው የፈተና ሂደት ጋር በተያያዘ በማያውቀው እና የእሱ ባልሆነ “ቲጅ የማርያም” በተሰኘ የፌስ ቡክ አካውንት ፈተናው እንዲስተጓጎል ቅስቀሳ አድርገሃል በሚል ይሰሩት እንጅ ከታሰረ በኋላ “ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አለህ?” በሚል መርምረውታል። በመጨረሻም “ቲጅ የማርያም” በሚል የፌስ ቡክ ገጽ ተማሪዎች እንዳይፈተኑ ቅስቀሳ አድርገሃል በማለት በደብረ ታቦር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ያቀረቡትና ቀጠሮ የተሰጠ ቢሆንም ተመልሰው በሽብር ወንጀል በዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ስለከሰስነው ፋይሉ ይዘጋልን በማለት ማዘጋታቸው ይታወሳል። ዞን ፖሊስ ከደብረ ታቦር ማ/ቤት ከተረከበ በኋላም በሽብር ወንጀል ክሱን ሲያስኬድ ቢቆይም በየመካከሉ ከደቡብ ጎንደር ዞን አንዳንድ አመራሮች በውስጥ “ትግሉን ተወው እና እንስማማ” የሚል ሽምግልና ተልኮበት፣ በጀመረው አማራዊ አንድነትን ያስቀደመ ትግሉን እንደሚገፋበትና የሚከፈለውን ሁሉ ለመክፈልም ዝግጁ ስለመሆኑ በመግለጽ አለመስማማቱን አስታውቆ እንደነበር ተሰምቷል። በደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የቀረበው አቶ ቢሰጥም እስካሁን የቀረበብኝ ማስረጃ ስለሌለ በነጻ ልለቀቅ ይገባኛል፤ ፍ/ቤቱ ይህን ካለፈው ደግሞ የዋስትና መብቴ ተብሮልኝ ከግፍ እስር እንድፈታ እጠይቃለሁ ስለማለቱ ተገልጧል። በዚህ ጥቅምት 10/2015 ረፋድ ላይ በደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርቦ በነበረው ችሎትም የዋስትና መብቱ ስለተጠበቀለት የተወሰነውን የ20 ሽህ ብር ዋስትና በመክፈሉ ከሰዓት በኋላ መፈታቱን ለማወቅ ተችሏል። በመጨረሻም ቢሰጥ አሰፋ በእስሩ ወቅት ድምጽ በመሆን ከጎኑ ላልተለዩት የሚዲያ ተቋማት፣ የማህበረሰብ አንቂዎች፣ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ተቆርቋሪ ወገኖች ሁሉ ላቅ ያለ ምስጋና ማቅረቡን አሚማ ለማወቅ ችሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply