You are currently viewing “በሽንፋ ግንባር በመከላከያችንና በአካባቢ የጸጥታ መዋቅር፣ በልዩ ኃይላችንና ሚሊሻችን እውነትም የአፄ ቴዎድሮስ ታሪክ የተደገመበት ዕድል ማየት የቻልንበት ነው።”  አቶ ደሳለኝ ጣሰው:- የም…

“በሽንፋ ግንባር በመከላከያችንና በአካባቢ የጸጥታ መዋቅር፣ በልዩ ኃይላችንና ሚሊሻችን እውነትም የአፄ ቴዎድሮስ ታሪክ የተደገመበት ዕድል ማየት የቻልንበት ነው።” አቶ ደሳለኝ ጣሰው:- የም…

“በሽንፋ ግንባር በመከላከያችንና በአካባቢ የጸጥታ መዋቅር፣ በልዩ ኃይላችንና ሚሊሻችን እውነትም የአፄ ቴዎድሮስ ታሪክ የተደገመበት ዕድል ማየት የቻልንበት ነው።” አቶ ደሳለኝ ጣሰው:- የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… መስከረም 4 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ኢትዮጵያን የማፍረስ አጀንዳና ተልዕኮ ያለው ጁንታ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ሽንፋ ንዑስ ወረዳ ላይ ነሀሴ 26/2013 ከጥዋቱ 12:00 ወረራና ቀጠናውን አተራምሶ ከተማውን አውድሞ ወደ መሀል በመግባት የቅማንትን ህዝብና ጽንፈኛ ቡድን ደጀንነት በመጠቀም ጎንደርና ጭልጋን ለመቆጣጠርና አገር የማፍረስ እሳቤውን እውን ለማድረግ አቅዶ ተኩስ ስለመክፈቱ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ተናግረዋል። አቶ ደሳለኝ ሲቀጥሉ ነገር ግን የአካባቢያችን የጸጥታ መዋቅር ሚሊሻችን ልዩኃይላችንና የመከላከያ ሰራዊታችን እውነትም የአጼ ቴዎድርስን ታሪክ የተደገመበት ዕድል ማየት የቻልንበት ነው ብለዋል። ከነሀሴ 26/2013 ጀምሮ አስከ ዛሬ መስከረም 3/2013 በተከፈተው ግጭት በ4 አቅጣጫ ሽንፋ ንዑስ ወረዳ የከበበ ቢሆንም አብዛኛው ሀይል እዚያው እንዲቀርና እንዲደመሰስ የተደረገበት ከፊሉ የተማረከበት ፣ ቁስለኛና የተወሰነ ኃይል አንጠባጥቦ ወደ ቲሀ ለመግባት ቢሞክርም ዙሪያውን ዝግ በማድረግ እስከ ሌንጫ ድረስ የቅማንት ህዝብና ጽንፈኛው ቡድን ተባብሮ ወደ ጦርነት አስገባለው ያለው ህልም እውን እንዳይሆን አቀጭጨነዋል ነው ያሉት። በዚህም ከ450 ያላነሰ ሰራዊት ተደምስሷል። ከ15 ያላነሰ ሠራዊት ተማርኳል ከ69 በላይ በራሳቸው መገናኛ የሰማነው ከባድ ቁስለኛ ወደ ቲሀ መሻገሩን መረጃው አለን ብለዋል። በሌላ በኩል ቁጥሩ ያልታወቀ በተኩስ መሀል በሽንፋ ወንዝ ለማምለጥ ሲሞክር በተደረገ መላላጥ በርካታ የሆነ ከፍተኛ ሀይል ወንዙ በመደምሰስ ከፍተኛውን ድርሻ መውሰድ መቻሉን የአይን እማኞችና መረጃ ያለ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ተደምሮ ከ600 በላይ እንበል እንጅ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኃይል መክኗል። ይዞት የገባው ኃይል በስሩ 600 ያለው ኃይል ወደ አምስት ሺ አለቃ ይዞ የገባ ቢሆንም አብዛኛውን ኃይል የመደምሰስ ስራ ተሰርቷል ብለዋል። ወደ ቲሀ ይዞት የወጣው ቁስለኛና ወስን ቁጥር ያለው ኃይል በማደራጀት መልሶ ለማስገባት ጥረት የማድረግ ስራ ቁስለኛውና ተዋጊው የደረሰበትን ጉዳት በማየት ለመግባት አንደበትና አቅም የሌለው መሆኑን ለመግለጽ በማወቃቸው በተለይ ሱዳን አካባቢ ያሉ እነ ጀነራል ፍሰሀ ማንጁስ አዲስ ሀይል አምጥቶ ፊት የገባው ሀይል ድል እያደረገ ነው እያሉ ዛሬም ያልሰለቻቸው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ለሰራዊታቸው እየነገሩ መልሶ እንዲገባ ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል ። እስከ መስከረም 3/2013 ድረስ ወራሪው ኃይል የቅማንት ጽንፈኛ ሽፍታና ህዝቡን ደጀን አድርጎ በመጠቀም የገባ ቢሆንም አልተሳካለትም ብቻ ሳይሆን እስከ ሌንጫ ቀበሌ ድረስ ተላላኪውን የሽፍታ ቡድን ጭምር ተገቢው ርምጃ ተወሰዶ ከፍተኛ ሀይል የመከነና የተደመሠሠ መሆኑንና የዚህ ቀጠና አይደፈሬነቱን አስመስክሯል ነው ያሉት። በተለይም ደግሞ ቀበሌዎችን ዘውዴ ባድማ ፣ ጉባይ ጀጀቢትና ሌንጫ ሙሉ በሙሉ እኛ በምንመራበት ደረጃ ከጸረ ሰላም ሀይል ነፃ የማድረግ ስራ በመስራት ጀብድ ተፈጽሟል ብለዋል። ቀሪው ኃይልም በየቁጥቋጦው እየተላላጠ ለሰራዊታችን እጅ እየሰጠ ነው ብለዋል። ትናንት የጁንታውን አስተሳሰብ የተሸከመ የማህበረሰብ ክፍልም ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ የመንግስትን ድጋፍ እየጠየቀ ለመሠባሰብ ጥረት እያደረገ ስለመሆኑ ተገልጧል። በአሁኑ ሰዓት የፖለቲካ አመራሩም ገብቶ ባለቤትና አብሮነትና ኢትዮጵያዊነት እንዳለ ሆኖ “የቅማንት ህዝብ ከአማራ ህዝብ የማይለይ ሆኖ ሳለ እንዴት ለጁንታ ተባባሪ ይሆናል?” የሚል በጸጸት የሚያነሳ አለ ይህም ብቻ አይደለም ህግን መሠረት ተደርገው የሚወሰዱ ርምጃወች እንደሚቀጥሉና የፖለቲካ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል ። የመከላከያ ሰራዊታችን ፣ ልዩ ኃይላችን ፣ ሚሊሻችን በአጠቃላይ የምዕራብ ጎንደር ህዝብና ወጣቱ የአመራር ስምሪት በሚሠጠው አግባብ በመደማመጥ ተልዕኮውን ለመፈፀም ያደረገው ርብርብ ከፍተኛ መሆኑንና ክብርና ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ ብለዋል። በመጨረሻም ከመንግስት ጎን ከመሠለፍ ይልቅ በተቃራኒ እንደ ጁንታው የሚያደናግሩ አመራርን ከአመራር ለመነጠል የሚያስቡ ቡድኖች በግርግር የራሳቸውን ጥቅምና ዕድል ለመጎናፀፍ የሚፈልጉ ስግብግብ ሌቦችና ባንዳወች በመኖራቸው በተግባራቸው እኩይ ተልዕኮ የሚፈጽሙ ማናቸውም አካላት ልክ እንደ ጁንታው ርምጃ እንወስዳለን ብለዋል ሲል የመተማ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply