በቀን ከ25 እስከ 30 የሚሆኑ ሰዎች የእብድ ውሻ በሽታ ህክምና አገልግሎትን ያገኛሉ ተባለ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እና በአጎራባች አከባቢዎች የእብድ ውሻ በሽታ ህክምና አገልግሎትን የሚያገኙበት ሁኔታ መኖሩ ተነግሯል፡፡

በማበረሰቡ ዘንድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የእብድ ውሻ በሽታን በተመለከተ የግንዛቤ መሻሻሎች መስተዋሉን በኢትዮጲያ የማህበረሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የእንስሳት ነክ ተመራማሪ እና አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር ይመር ሙሉጌታ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ እና በአጎራባች አከባቢዎች እንዲሁም ከሆስፒታሎች በሚላኩ ሪፈራሎች አማካኝት፣ በአመት ከ45 እስከ 50 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች የእብድ ውሻ በሽታ የህክምና አገልግሎትን እንደሚያገኙ ተነግሯል፡፡

የእብድ ውሻ በሽታ በጤና ተቋማት ላይ የህክምና አገልግሎት ማግኘት እንደሚቻል የተገለጸ ሲሆን፤ በውሻ የንክሻ አደጋ አጋጥሟቸው እንዲሁም ከስጋት አንጻር ወደ ኢስቲዩቱ የሚሄዱ ዜጎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ህመሙ በህክምና የሚድን ቢሆንም የህክምና ክትትል ካልተደረገ ግን በሰዎች ላይ የህይወት ማለፍን እንደሚያስከትል ተመላክቷል፡፡

በእሌና ግዛቸው

መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply