በቀን ውስጥ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ዝዉዉር በሳንቲም ፔይ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገለፀ።በኢትዮጵያ የክፍያ ስርዓት ውስጥ ኦፕሬተር ሆኖ ለመስራት ከአንድ አመት በፊት ስራ የጀመረው…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/QhiX-PyqcbG65XZyTjzQnGB_d8GxlX_RKuYQmGisDfIBrcHH38OyW5C4j_R0bsDlFB4wKlQTeAevt92zxTLNPF5yTtdOtg8Me8FW4_AsoSghf7B-NS0aDJCQvjIo96RRc_bVQbWy6CTt-GKuoaJH-BkZln16GZr2nZ-dBM4w46DQbLi9FmR7YDHBkFnFRiZyP-EX37AAuP1wOrqsC1XVqOzexy39WP1EfduHlsFl9UMxVTbkzbTpFEd5l0DGbK6KsUpPIEiki1Z6vYWd-GPOGbsC3Jq2NAFFO34BRDhaRF6oPWtPEukZ1DJN3Um8BnI-4j3blxtCxpIGPxhJArk_yg.jpg

በቀን ውስጥ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ዝዉዉር በሳንቲም ፔይ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገለፀ።

በኢትዮጵያ የክፍያ ስርዓት ውስጥ ኦፕሬተር ሆኖ ለመስራት ከአንድ አመት በፊት ስራ የጀመረው ሳንቲም ፔይ፤ በቀን ውስጥ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ በሳንቲም ፔይ አማካኝነት የገንዘብ ዝዉውር እየተደረ እንደሚገኝ ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ትንሳኤ ደሳለኝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልፀዋል።

በሶስት ቴክኖሎጂዎች ፤ ፖስ (ተንቀሳቃሽ የክፍያ መተግበሪያ)፣ ዩኒፋይድ ፔይመንት ኢንተርፌስ (ዩ ፒ አይ) (ባንኮችን የሚያስተሳስር የክፍያ ስርዓት) እና ፔይመንት ጌትዌይ (በኢንተርኔት የሚደረጉ ክፍያዎችን የሚያስተሳስር) በተባሉ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶች አማካኝነት የገንዘብ ዝዉዉሩ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤ ያደረገዉ ሳንቲም ፔይ ሶሉሽን አ.ማ ከዘጠኝ ባንኮችና ከቴሌብር ጋር ስራ መጀመሩ ተገልፆ በቅርቡ ከአውሮፓ ባንኮች ጋር ለመስራት ስምምነት መደረጉ ተገልጿል።

የውጭ ምንዛሬን ከመቀነስ አኳያ ብዙ ስራ እየተሰራ እንደሆነ የሚያነሱት ስራ አስፈፃሚው፣ አሁን ላይ ባንኮች ለፖስ የሚያወጡትን ዋጋ በ20 በመቶ በማሳነስ ትልቅ የውጭ ምንዛሬ ማዳን እንደተቻለም ገልፀዋል።

ሳንቲም ፔይ ከገንዘብ ንክኪ ነጻ የሆነ ዲጂታል እና የዘመናዊ ግብይት ተጠቃሚ የሆነ ማህረሰብን ዓላማ እንዳለዉ ያሳወቀ ሲሆን አሁን ላይ የክፍያ ሥርዓትን ለማዘመን እና ተደራሽነቱን ወደ ክልሎች ለማስፋት እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በለዓለም አሰፋ
ጥር 06 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply