በቀይ ባህር አካባቢ ያለዉን ዉጥረት ማረጋጋት የሚቻለዉ ጋዛ ሰላም ከሆነች ብቻ ነዉ ተባለ፡፡

አንድ የየመን ባለስልጣን እንደገለጹት፣ በቀይ ባህር አካባቢ ሰላም ሊሰፍን የሚችለዉ በጋዛ ዘላቂ ሆነ የተኩስ አቁም ሲኖር ብቻ ነዉ ብለዋል፡፡

ባለስልጣኑ ይህንን ያሉት አሜሪካ በእስራኤል ወደ ተያዙ አካባቢዎች የምትልከዉን ድጋፍ ለመጠበቅ የባህር ሃይሏን በቀይ ባህር ዙሪያ ለማሰማራት ማስታወቋን ተከትሎ ነዉ፡፡

የዓለም መንግስታት ድርጅት የባህር ሃይሎች ወደ ቀይ ባህር ቢዘምቱ እና በቦታዉ ላይ ቢሰፍሩ ለእስራኤልም ሆነ ለክልሉ መንግስት አልያም በእስራኤል ለተያዙ የፍልስጤም አከባቢዎች ምንም ዓይነት ደህንነትን መስጠት አይችሉም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በቦታዉ ላይ ያለዉን ከፍተኛ ዉጥረት ሊያረጋጋ የሚችለዉ ጉዳይ፣ በጋዛ የሚደረግ ዘላቂ የተኩስ አቁም ሲኖር ብቻ ነዉ ያሉም ሲሆን ፤ ለቀይ ባህር አካባቢ መረጋጋትን ሊያመጣ የሚችለዉ ብቸኛዉ መንገድ የጋዛ ሰላም መሆን ነዉ ብለዋል፡፡

በእስራኤል እና ጋዛ ጦርነት እስካሁን ድረስ ከ18ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን የተገደሉ ሲሆን ከ50ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ መጎዳታቸዉን ፕሬስ ቴሌቭዥን ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ታህሳስ 04 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply