You are currently viewing በቀይ ባህር የሰፈነው ያለመረጋጋት በኢትዮጲያ ቡና ገበያ ላይ ስጋት ፈጠረ።

በቀይ ባህር የሰፈነው ያለመረጋጋት በኢትዮጲያ ቡና ገበያ ላይ ስጋት ፈጠረ።

ከሰሞኑ በቀይ ባህር እየተፈጠረ ባለዉ የፀጥታ ስጋት ወደ ዉጪ የሚላከዉን የቡና መጠን ሊቀንስ ይችላል መባሉን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

የኢትዮጵያን ቡና ለአለም አቀፍ ገበያ ለማስታዋወቅ በተዘጋጀ ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ ናቸው ይህንን ስጋት የገለፁት።

በሀገር ውስጥ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ለቡና ምርት ሂደቱ ስጋት እንዳልፈጠረም ሰምተናል።

ዳይሬክተሩ ከጣብያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታም በሀገር ዉስጥ ለዘርፉ ከፀጥታ አንፃር ስጋት ይኖር እንደሆነ ተጠይቀዉ ” በሀገር ዉስጥ ከፀጥታ አኳያ ስጋት የለብንም” ብለዋል።

በሀገር ዉስጥ የኮንትሮባንድ ንግድ ላይ ችግሮች መቀጠላቸውን አንስተው እንቅስቃሴውን ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት እንዳልተቻለ ተናግዋል።

ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች በአንፃራዊነት ከፍተኛ ቡና ተጠቃሚ አገር መሆኗ የተጠቆመ ሲሆን 50 በመቶ የሚሆነው ምርት ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚዉል መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግዋል።

ያለ ህጋዊ ፍቃድ ቡና መሸጥም ሆነ መላክ ስለማይቻል በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚገኙ ግለሰቦችን ከፀጥታ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ለህግ የማቅረብ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ነግረውናል።

በአቤል ደጀኔ
የካቲት 04 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply