
በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለ ማርያም ጌታቸው ይባሉ የነበሩ፣ በሕገወጥ መንገድ ከተሾሙት አንዱ የሆኑና “አቡነ አቤል የምእራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ” በሚል የተሾሙ ናቸው። በሀገረ ስብከቱ ዋና ከተማ አሰበ ተፈሪ (ጭሮ) በምትገኘው ደብረ ጽዮን ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን መንበረ ጵጵስናን በኃይል በመስበር፣ ምዕመናኑን በጥይት፣ በቆመጥና በአስለቃሽ ጭስ ጭምር ከቤተክርስቲያኗ በማባረር የከተማው ልዩ ኃይል አዲሱን ተሿሚ ማስገባታቸው ይታወቃል። አዲሱ ተሿሚ ላለፉት ሦስት ቀናት ብቻቸውን ከቆዩ በኋላ ዛሬ ጧት ምእመኑ ሙሉ በሙሉ ከቤተክርስቲያን መቅረቱን ሲያዩ “ነገሩ እንዲህ የሚሆን ፈጽሞ አልመሰለኝም። በእኔ ምክንያት ቤተክርስቲያኔ በመዘጋቷ አዝኛለሁ” ብለው ማልቀሳቸውን እና ብቻቸውን ጠፍተው ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን አጠገባቸው …የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል። የት እንዳረፉ የምታውቁ ኦርቶዶክሳውያን የጨለማው ቡድን ሳያፍናቸው ለንሰሐ አብቋቸው። በአሁኑ ሰዓት በአሰበ ተፈሪ (ጭሮ) ከተማ በሚገኙ አምስት አብያተ ክርስትያናት ምንም አይነት መንፈሳዊ አገልግሎት እየተሰጠ አይደለም። ጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post