በቀጣይ ሁለት ሳምንት ጃንሜዳ ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንደሚመለስ ወ/ሮ አዳነች ገለፁ

በቀጣይ ሁለት ሳምንት ጃንሜዳ ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንደሚመለስ ወ/ሮ አዳነች ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቀጣይ ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ጃንሜዳ ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንደሚመለስ ወ/ሮ አዳነች አዳነች አቤቤ ገለፁ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ከወጣቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች እና አርቲስቶች ጋር ጃንሜዳን አፅድተዋል፡፡

የከተማዋ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ገፃቸው እንዳስታወቁት ጃንሜዳ ለጥምቀት በዓል ዝግጁ እንዲሆን የሚሰራው ስራ በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል።

በዓሉ ድምቀቱን ፣ እሴቱን እና ውበቱን በጠበቀ አግባብ እንዲከበርም እየሰራን ነው ብለዋል ወ/ሮ አዳነች።

በቀጣይ ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ጃንሜዳ ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንደሚመለስ ወ/ሮ አዳነች ጠቁመዋል፡፡

የአትክልት መገበያያ ስፍራዎችን በሌሎች አካባቢዎች ተደራሽ የማድረግ ስራዎች ጎን ለጎን እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ በጃንሜዳ የሚገኙ ነጋዴዎች ከነገ ጀምሮ ወደ ሀይሌ ጋርመንት ሙሉ በሙሉ ይሸጋገራሉ ብለዋል፡፡

ነጋዴዎች ወደ ጋርመንት በሚዘዋወሩበት ሁኔታዎች ዙሪያ ምክትል ከንቲባዋ በጃንሜዳ የሚገኙ ነጋዴዎችን ተዘዋውረው አነጋግረዋል፡፡

በቦታው የነበሩ ነጋዴዎች እንደገለጹት የከተማ አስተደዳሩ ላደረገው ድጋፍ ሁሉ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ከነገ ጀምሮ ከተማ አስተዳደሩ በሚሰጠን አቅጣጫ መሰረት በተዘጋጀው ቦታ ለመዘዋውር ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

ስራው የጋራ ነው ብላችህ አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ ባለድርሻ አካላት ሁሉ ላመሰግን እወዳለሁ ብለዋል።

The post በቀጣይ ሁለት ሳምንት ጃንሜዳ ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንደሚመለስ ወ/ሮ አዳነች ገለፁ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply