በቀጣይ ለውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ከ5 መቶ ሺህ ባላይ ዜጎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተባለ

በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጲያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ፕሮጀክት ጽፈት ቤት ሃላፊ ብርሃኑ አለቃ እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ጨምሮ ስራ እና ሰራኛን በተመለከተ ከ23 በላይ አገልግሎቶችን ይሰጣል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ ስራ ፈላጊ ዜጎች ደህንነታቸው ተጠብቆ በህጋዊ መንገድ ያለምንም የገንዘብ ክፍያ ወደ ውጭ ሀገራት ለማሰማራት ያለመ ነው ተብሏል።

በ2014 ዓመት ላይ 40 ሺህ ስራ ፈላጊ ዜጎች ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ የተሰማሩ መሆኑን እና በ2015 ዓም እስከ 9 ወር ድረስ አገልግሎቱ በማንዋል ይሰጥ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

6 ወራትን ይፈጅ የነበረው አገልግሎቱ የቴክኖሎጂን አገልግሎት በመጠቀም አሰራሩ በ10 ደቂያ ውስጥ እንዲያልቅ መደረጉ ተመላክቷል፡፡

በመሆኑም በ6 ወራት ውስጥ ለ261 ሺህ ዜጎች በውጭ ሀገራት የስራ እድሎች መመቻቸቱ ተነግሯል።

በአሁኑ ወቅት ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ የሚሰማሩ ዜጎች የሰለጠኑ እና በከፊል የሰለጠኑ መሆናቸውን እና ከሚሄዱበት ሀገር ጋር መንግስት የሁለትዮሽ ውል እንደሚዋዋል ተናግረዋል፡፡ ይህም በዜጎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቀነስም ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለ5 መቶ ሺህ ዜጎች ወደ ውጭ ሀገራት የሥራ እድል የማመቻቸት እቅድ በመያዝ እየሰራ እንደሚገኝ እና ከሌሎች ተቋማት ጋር በሲስተም እንዲተሳሰር መደረጉ ተመላክቷል።

የኢትዮጲያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ፕሮጀክት በ2015 ዓምት የተጀመረ መሆኑን የተናገሩት አቶ ብርሃኑ በአሁኑ ወቅት ስራ ፈላጊ ዜጎችን የሚቀበሉ የውጭ ሀገራት ላይ ፍላጎቶች መጨመራቸውን ተከትሎ ወደ ሀገራቱ ለስራ የሚላኩት ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል ብለዋል፡፡

በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አማካኝነት ለስራ ወደ ውጭ ሀገራት ከተላኩ ዜጎች አብዛኞቹ ሴቶች ቢሆኑም ወንዶችም ተሳታፊ እየሆኑ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው
መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply