በቀጣይ ዓመት ብሔራዊ መታወቂያ የሌላቸው ነጋዴዎች የንግድ ፈቃድና ምዝገባ አገልግሎት አያገኙም እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የንግድ ፍቃድ ምዝገባ አገልግሎት እስካሁን በነበረው አሰራር የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ያላቸው ሰዎች አገልግሎቱን አንደሚያገኙ እና ለቀጣይም በዛው እንደሚገለገሉ ተነግሯል፡፡

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የላይሰንሲንግ እና ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጅራታ ነመራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እነደተናገሩት የተሰራጨዉ መረጃ ስህተት ነዉ ብለዋል፡፡
ከሁሉም ተቋማት ጋር በመተባበር ለንግድ ስራ ፈቃድ አገልግሎት የሚያስፈልግ ግብአቶች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣የግብር ክሊራንስ እና በሰነድ የሚረጋገጡ ነገሮችን በሙሉ ከተቋማቶቹ በቀጥታ ማግኘት የሚቻልበትን አሰራር እየዘረጋን እንገኛለል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አሰራሩ ተግባራዊ ሲሆን መረጃዎቹን ከተቋማቱ ማግኘት ስለሚቻል ሰዎች አገልግሎት ሲፈልጉ ጥያቄ የማቅረብ ስራ ብቻ እንደሚኖርባቸው አንስተዋል፡፡

አሁን ላይ አሰራሩን ተግባራዊ ለማድረግ የሚቀሩ ስራዎች እንዳሉት የገለፁት መሪ አስፈፃሚው እስከቀጣይ አመት ተጠናቆ ስራ ላይ ይውላል የሚል እቅድ መያዙን ተነግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው
መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply