በቀጣይ 10 ቀናት በአንዳንድ የአገሪቱ አከባቢዎች የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ይችላል ሲል የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ አስጠነቀቀ።

የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አህመዲን አብዱልከሪም ለአሀዱ እንዳሉት በተያዘው የክረምት ወራት በኢትዮጵያ አብዛኛው አከባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በስርጭት የተስፋፋ ዝናብ ይኖራል ።

የክረምት ዝናብ መፈጠር መንስኤ ሊሆኑ የሚያስችሉ የአየር ሁኔታ ክስተቶች እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ ያነሱት አቶ አህመዲን በሰሜን ምዕራብ፤ በምእራብና መካከለኛ አከባቢዎች የተሻለና መጠነኛ ዝናብ እንደሚኖር ጠቁመዋል ።

በኢትዮጵያ በሌሎች ቦታዎች በተለይም የክረምት ተጠቃሚ አከባቢዎች ላይ የሚኖረው የዝናብ መጠን እየተጠናከረ እንደሚሄድ የተናገሩት አቶ አህመዲን በሚቀጥሉት 10 ቀናት በአንዳንድ አከባቢዎች  ከሚጠናከረው የደመና ክምችት ጋር ተያይዞ ከባድ ዝናብ የሚኖር ሲሆን በተለይ የአዋሽ የጣናና ሌሎች ወንዞችም መሙላታቸውን ተከትሎ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተቁመዋል ።

ከአዲስ አበባ ከተማ በተጨማሪ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችም ከጥንቃቄ ባለፈ ውሀ እንደልብ እንዲዘዋወር  ተፋሰስን የማፅዳት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል ።

ቀን 21/11/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply