በቂ በጀት ባለመኖሩ በትግራይ ክልል የሚፈለገውን ያህል ድጋፍ ማድረግ እንዳልተቻለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀይ መስቀል ማህበር አስታወቀ፡፡

ማህበሩ በትግራይ ክልል በህግ ማስከበር ዘመቻው ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ እንዲሁም በመተከል ዞን  እርዳታን ለሚሹ ዜጎች ድጋፍ  እያደረገ  ስለመሆኑ ገልጻል፡፡

የማህበሩ የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ሰለሞን አሊ ለአሀዱ እንደተናገሩት ማህበሩ ሰው ሰራሽና ተፍጥሯዊ አደጋዎች በሚያጋጥሙ ጊዜ ለዜጎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረግ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡በትግራይ ክልል እንዲሁም በመተከል ዞን የመጠጥ ውሀን በማቅረብ፤ የህክምና ቁሳቁስ  የአምቡላንስ አገልግሎት በመስጠት እንዲሁም ምግብና ምግብ ነክ የሆኑ ድጋፎች እየተደረገ መሆኑንን ተናግረዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ማህበሩ ከ200 በላይ ቅርጫፎች እንዳሉት የተናገሩት አቶ ሰለሞን  ጉዳት ለደረሰባቸው  ዜጎች የሚፈለገውን ያህል እርዳታና ድጋፍ ለማድረግ የአቅም ማነስ ወይም በቂ በጀት አለመኖር እንቅፋት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ማህበሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ በመተከል፤ ኮንሶ፤ አፋር፤ ጎንደር እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ባደረገው ዳሰሳም 2.5 ሚሊየን እርዳታ የሚሹ ዜጎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡ መልሶ ማቋቋም የሚስፈልጋቸው ዜጎች ደግሞ 5 ሚሊየን መሆናቸውን ማህበሩ ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ማረጋገጡን ነው የገለፁት፡፡

እርዳታ ከሚሹ ዜጎች ጋር ሲነጻጸር ማህበሩ 5ሺ ብቻ ለሚሆኑት ተደራሽ ማድረጉ ካለው ተረጂ  ብዛት አንጻር  በቂ ነው ለማለት እንደማያስደፍር ተናግረዋል፡፡ መንግስት ከ70 እስከ 80  በመቶ በላይ የመሸፈን አቅም እንዳለው የተናገሩት ዳይሬክተሩ አስፋለጊውን ድጋፍ በማድረግ ሊሰራ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ማህበረሰቡም ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶችን እንዲሁም በገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ቀን 22/06/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply