በቅርቡ በራሱ ሰራተኞች ጉዳት የደረሰበት የአይደር ሆስፒታል የላብራቶሪ ክፍል አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተነገረየሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገ/እግዚአብሔር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/CMciIcfxlR1M19B6c3FZvzhXamV5a-56rJsJgNhLiq2K4xsxV5XfzEFW6IFFgRpx-yUY2C1PrSdy_z5S6D8zqvx0hJRPRvcg0oAvI28G_NcTD4UxtZWGf2Jx4h9NhVp5nBMX_vO6klTj5J1TKdasz6ftadzSJuuHXW8sfdFmNsuBaR8kslQ6xQOLa3nHPtKfsRgZI45WV9EW2mQBsLWumq48gGur-nHf2xUXQfIIGzXzK5KVjpXaRxg9Iio0AQD_aVleqqflXVAGUnFUbls0gW8-3Ow1Qb6zByyweWH7yjG3EtuAMeSSjyFZm-NYxTMSD4eaEksjgMSMAKzGbsPWzA.jpg

በቅርቡ በራሱ ሰራተኞች ጉዳት የደረሰበት የአይደር ሆስፒታል የላብራቶሪ ክፍል አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተነገረ

የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገ/እግዚአብሔር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ማሽኑ በተለያዮ አቅጣጫዎች ውድመት ደርሶበት  ለሁለት ሳምንት ያህል ከአገልግሎት ውጪ እንደነበር ተናግረዋል።

ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች 4 ግለሰቦች መሆናቸውን እና በቁጥጥር ስር ዉለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹም ማሽኑ በነበረበት የስራ ክፍል ላይ ተመሳሳይ የስራ ድርሻ የነበራቸው መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል ።

እስካሁንም ድርጊቱ ለምን እንደተፈፀመ የተደረሰበት ነገር አለመኖሩን እና አሁንም በምርመራ ላይ እንደሆነ አንስተዋል ።

ድርጊቱ የተፈፀመው መጋቢት 21 ለሊት ሲሆን በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ያለው የህክምና መሳሪያ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር የሚታወስ ነው።

ሐመረ ፍሬው
ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply