በቅርቡ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት መንገደኛ ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ሙስናና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ናቸው ተባለ፡፡

ድርጊቱን የፈፀሙት የኮሚሽኑ ሰራተኞችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተነግሯል ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰሞነኛና በአየር መንገዱ እንቅስቃሴ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል ።

ዋና ስራ አስፈፃሚው በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ለሚፈፀሙ ወንጀሎች አየር መንገዱን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ማድረግ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከአየር መንገዱ በተጨማሪ፣ ኢሚግሬሽን ፣ጉምሩክ ፣ብሄራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ፌደራል ፖሊስ የራሳቸው ድርሻ አላቸው ነው ያሉት።

በቅርቡ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት መንገደኛ ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ሙስናና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች እንጅ የአየር መንገዱ ሰራተኞች አይደሉም ብለዋል አቶ መስፍን።

በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ መሰል ድርጊቶች እንዳይፈፀሙ ከእነዚህ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሰራም ተናግረዋል ።

በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከ 3 ሺህ በላይ የደህንነት ካሜራዎች ሰምተናል ።

የተከበራችሁ አድማጮቻችን በወቅታዊ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዙሪያ የተሰጡ ምላሾችን አካተን በኢትዮ አመሻሻችን በስፋት የምንመለስበት ይሆናል።

በአባቱ መረቀ

መጋቢት 09 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply