You are currently viewing በቅርቡ ከአስከፊ መንግስታዊ እገታ እና እስር በ18 ሽህ ብር ዋስትና የተለቀቀው ታጋይ አሸናፊ አካሉ ከስራው መሰናበቱ ተገለጸ፤ አሸናፊም ጉዳዩን በተመለከተ “ግፍ ሞልቶ ፈሰሰ” ሲል ገልጾታል…

በቅርቡ ከአስከፊ መንግስታዊ እገታ እና እስር በ18 ሽህ ብር ዋስትና የተለቀቀው ታጋይ አሸናፊ አካሉ ከስራው መሰናበቱ ተገለጸ፤ አሸናፊም ጉዳዩን በተመለከተ “ግፍ ሞልቶ ፈሰሰ” ሲል ገልጾታል…

በቅርቡ ከአስከፊ መንግስታዊ እገታ እና እስር በ18 ሽህ ብር ዋስትና የተለቀቀው ታጋይ አሸናፊ አካሉ ከስራው መሰናበቱ ተገለጸ፤ አሸናፊም ጉዳዩን በተመለከተ “ግፍ ሞልቶ ፈሰሰ” ሲል ገልጾታል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በባህር ዳር ለሁለት ሳምንት ገደማ በመንግስት የጸጥታ አካላት ታፍኖ ደብዛው ጠፍቶ ከሰነበተ በኋላ ወደ ፍ/ቤት ቀርቦ በተደረገ የሳምንታት ክርክር ከእስር የተፈታው ታጋይ አሸናፊ አካሉ ከስራው ተሰናብተሃል የሚል ደብዳቤ ተሰጦታል። አሸናፊ አካሉም በበኩሉ “የብአዴንን የግፍ ግፍ ጉድ፣እኔን አግተው ከስራዬ አሰናብተውኛል!!! ግፍ ሞልቶ ፈሰሰ…” ሲል ገልጧል። የመንግስት ግዥና ንብረት ኦዲት ክትትልና ጥናት መረጃ ትንተና ዳይሬክቶሬት ውስጥ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ስልጠናና ሙያዊ ድጋፍ ባለሙያ የሆኑት ሠራተኛ ከስራ ቦታቸው አለመገኘታቸውን በደብዳቤ እንዳሳወቁ በመግለጽ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ጥሪ ማስታወቂያ ተደረጉልዎት መጥተው ሪፖርት አላደረጉም በሚል ከየካቲት 24/2015 ዓ.ም ጀምሮ በራስዎ ፈቃድ ከሥራ የተሰናበቱ መሆኑን እንገልጻለን የሚል ደብዳቤ ከተቋሙ የተሰጠው መሆኑን ለመመልከት ተችሏል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply