በቅርቡ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የወጣባቸው ቁሳቁሶች በማይካድራ ለተፈናቃዮች ድጋፍ ተደርጓል ሲል የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በጸጥታ ችግር ሳቢያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ተፈናቅለዋል፡፤ አሀዱም በቤኒሻንጉልና በሌሎች አከባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚደረገው ድጋፍ ምን ይመስላል ሲል ጠይቋል፡፤

በሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የህጻናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ኦሞድ ለአሀዱ እንደገለጹት ሚኒስቴሩ በሀገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች ቁሳቁስና ምግብ እንዲሁም የስነ ልቦና ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፤

በዚህም በማይካድራ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የወጣባቸው ቁሳቁሶችና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ደግሞ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል ተብሏል፡፤

ከቁሳቁስ ድጋፍ ባለፈ በችግር ውስጥ የሚገኙትን ለመደገፍና ለመለየት በሰላም ሚኒስቴር በተደረገው የማደራጀት ስራ የስነልቦና ድጋፍ እየተሰጣቸው መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል፡፤ በጸጥታ ችግር ሳቢያ በቤኒሻንጉል የታሰበውን ያህል የስነልቦና ድጋፍ አለመሰጠቱን ዴኤታዋ ገልፀው በአማራና በሌሎች አከባቢዎች ግን የታሰበውን ያህል እየተሰራ ነው ብለዋል፡፤

ቀን 19/11/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply