በቅርቡ ወደ ሀገር ዉስጥ እንዳይገቡ በታገዱት ሸቀጦች በዓመት ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ይደረግ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ገልጸዋል፡፡በመንግስት የዶላር ፍቃድ ወደ ሀገር…

በቅርቡ ወደ ሀገር ዉስጥ እንዳይገቡ በታገዱት ሸቀጦች በዓመት ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ይደረግ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ገልጸዋል፡፡

በመንግስት የዶላር ፍቃድ ወደ ሀገር ዉስጥ ይገቡ የነበሩ ወደ 6 ሺህ የሚጠጉ ሸቀጦች የነበሩ ሲሆን ከነዛ ዉስጥ 38ቱ ሸቀጦች ናቸዉ ወደ ሀገር ዉስጥ እንዳይገቡ የታገዱት ብለዋል፡፡

ለነዚህ ሸቀጦች ወደ ሀገር ዉስጥ መግባት መከልከል አራት ምክንያቶችን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ እነሱም፤

-አንደኛዉ ወደ ሀገር ዉስጥ የሚገቡት እነዚህ ሸቀጦች ወደ ሀገር ዉስጥ ከሚገባዉ ማዳበሪያ ጋር እኩል ዋጋ አላቸዉ፡፡

-ሁለተኛዉ ለሀገር ዉስጥ ምርት ዕድል ለመስጠት ታስቦ መሆኑን እና የፍራፍሬ ጭማቂ ፣ ሳሙና እንዲሁም የታሸገ ዉሃ ሳይቀር ወደ ሀገር ዉስጥ ይገባል ስለዚህ እነዚህን በሀገር ዉስጥ ምርት ለመተካት ታስቦ ነዉ፡፡
-ሶስተኛዉ ሙሉ በሙሉ እንኳን ባይሆን በከፊል ለጥቁር ገበያ የተጋለጡ በመሆናቸዉ ነዉ፡፡

-አራተኛዉ እና የመጨረሻዉ ደግሞ እነዚህ ሸቀጦች ‹‹መሰረታዊ›› አይደሉም፡፡ ወደ ሀገር ዉስጥ ለመግባት ለጊዜዉ ቢታገዱ ወይም ቢዘገዩ የሚጎዱ ባለመሆናቸዉ ነዉ፡፡

እነዚህን ሸቀጦች ባለማስገባታችን እንደ ሀገር ከምናጣዉ የምንገኘዉ ይበልጣል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ፤

እነዚህ ሸቀጦች ባለመግባታቸዉ የሚጎዱ ሰዎች የሉም ማለት ሳይሆን ‹‹ዉስኪ እያስገባን ማዳበሪያ ለማስገባት እንዳንቸገር ነዉ›› ብለዋል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ህዳር 06 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply