በቆላ ተንቤን የሚገኘው የጁንታው የመጨረሻ ምሽግ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል          አሻራ ሚዲያ      ህዳር 27 / 2013 ዓም ባህር ዳር በቆላ ተን…

በቆላ ተንቤን የሚገኘው የጁንታው የመጨረሻ ምሽግ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል አሻራ ሚዲያ ህዳር 27 / 2013 ዓም ባህር ዳር በቆላ ተን…

በቆላ ተንቤን የሚገኘው የጁንታው የመጨረሻ ምሽግ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል አሻራ ሚዲያ ህዳር 27 / 2013 ዓም ባህር ዳር በቆላ ተንቤን የሚገኘው የጁንታው የመ ጨረሻ ምሽግ በሀገር መከላከያ ሰራዊት በሶስት አቅጣጫ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደበት እንደሚገኝ ተገለጸ። በቆላ ተምቤን የጁንታውን አመራር ለመያዝ የሚ ደረገውን ዘመቻ እየመሩ ያሉት በመከላከያ ሰራዊት የ31ኛ ክፍለ ጦር ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ኮሎኔል ሻምበል በየነ እንደገለጹት፤ ከመቀሌ ቢሮው ለቆ የሸሸው የጁንታው አመራር በቆላ ተንቤን የመጨረሻ ምሽጉ ላይ ይገኛል። የመከላከያ ሰራዊትን የጁንታውን የመጨረሻ ምሽግ በተለያዩ አቅጣጫዎች ከቦ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። ቆላተምቤን ወርቅ አምባ ከተማ ላይ የመጨረሻ ምሽጉን ያደረገውን የጁንታውን አመራር ለመያዝ አሊያም ለመደምሰስ መከላከያ ሰራዊት በመረጃ የተደገፈ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል ያሉት ኮሎኔል ሻምበል፤ ከአድዋ መስመር የመጣው ሰራዊት አካባቢውን ለመቆጣጠር እየገሰገሰ እንደሆነ እና ከሃውዜን እና መቀሌ መስመር ያለውም ወደ ቦታው በከፍተኛ ወኔ እየተጠጋ እንደሚገኝ ገልጸዋል። መከላከያ ሰራዊቱ ወርህ የሚባል ትልቅ ወንዝ መሻገር አይችልም በሚል አካባቢ የጁንታው ታጣቂዎች ማጥቃት ቢፈጽምም ሰራዊቱ ወደ አካባቢው ተጠግቶ ከወርቅ አምባ 10 ኪሎ ሜትር ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል። እንደ ኮሎኔል ሻምበል ከሆነ፤ በቆላ ተምቤን ወርቅ አምባ አካባቢ የመሸገው ጁንታው በምድር ከሚወሰድበት እርምጃ ባለፈ በአየር ጭምር እርምጃ ተወስዷል። በአየርና በድሮን አውሮፕላኖች በተወሰደ እርምጃ ወርቅ አምባ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ሰባት የጁንታው ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ወድመዋል። ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply