በቆዳ ቀለሜ ምክንያት እንክብካቤ ተነፈገኝ ያለችው ሀኪም በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወቷ ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በአሜሪካ ኢንዲያና ነዋሪነቷን ያደረገችው ጥቁር አሜሪካዊቷ የጤና ባለሙያ በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል፡፡ባለሙያዋ በኮቪድ-19 ምክንያት ሆስፒታል ብትገባም በቆዳ ቀለሟ ምክንያት ዶክተሮች ተገቢውን እንክብካቤ እንዳላደረጉላት ስትናገር ቆይታለች፡፡ሱዛን ሙር የተሰኘችው ሐኪም ከኢንዲያና ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ውስጥ በለቀቀችው ቪዲዮ እንክብካቤ ለማግኘት ዶክተሮችን ትለምን እንደነበር ተነግሯል፡፡

ዩኒቨርስቲው የቀረበበትን ክስ እንደሚመረምረው የገለፀ ሲሆን ሆስፒታሉም ህይወቷ በማለፉ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡የ52 ዓመቷ ዶክተር ሙር በሌላ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና ላይ እያለች ነው ህይወቷ ያለፈው፡፡ሆስፒታሉም ዘርን መሠረት ያደረገ እንክብካቤ መንፈግ እንደማይፈቅድ አስታውቆ በቀረበው ክስ ላይ ምርመራ እንደሚያከናውን ገልፃል፡፡ ቢቢሲ

**************************************************************************

ቀን 17/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply