በቋሪት ወረዳ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በሰብል እና በእንስሳት ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 12 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራ…

በቋሪት ወረዳ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በሰብል እና በእንስሳት ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 12 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ጐጃም ዞን ቋሪት ወረዳ በዛንቢት ዝጉዳ ቀበሌ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ የበርካታ አርሶ አደሮች የመኸር፣ የመስኖ ሰብሎች እና በእንስሳት ላይ ከባድ ጉዳት ማድርሱን ተጐጅ አርሶ አደሮች ተናግረዋል። የዛንቢት ዝጉዳ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያረጋል ታደሰ እንዳሉት በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በ190 አርሶ አደሮች በስንዴ ፣ በገብስ፣በጤፍ፣ በባቄላ እና በድንች ስብሎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን ገልጸዋል። አያይዘውም አደጋው በተደጋጋሚ እየተከሰተ አርሶ አደሮችን ተስፋ እያስቆረጠ ነው ብለዋል፡፡ መንግስትም ሆነ የአካባቢው ማኅበረሰብ የተለያየ ድጋፍ ቢያደርግልን ሲሉ አቶ ያረጋል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ከተጐጅ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ቢተው ሽታው በበኩላቸው አካባቢው ወይናደጋ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የመኸርና የመስኖ ሰብሎች ሙሉ በሙሉ ያልተሰበሰቡ በመሆኑ በተከሰተው በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በሰብልና በእንስሳት ላይ ጉዳት ደረሶብናል ብለዋል፡፡ የዛንቢት ዝጉዳ ቀበሌ ግብርና ልማት ጣቢያ ተወካይ ኃላፊ አቶ ዘለቀ ያረጋል እንዳሉት በተለያዩ ሰብሎች ከተሸፈነው 837 ሄክታር መሬት መካከል 562ቱ ሄክታር መሬት የሰብል ስብሰባ የተካሄ መሆኑን ገልጸው፤ 275ቱ ሄክታር መሬት ደግሞ ታህሳስ 10/ ቀን/ 2014 ዓ.ም በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ ተጐድቷ ብለዋል ሲል የቋሪት ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ነው የዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply