በቋራ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች እና ነጋዴዎች ያመረቱበት እና ገዝተው የሚሸጡበት የአኩሪ አተር የሽያጭ ዋጋ ካወጡት ወጭ ጋር የተመጣጠነ ስላልሆነ የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲያፈላልግ…

በቋራ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች እና ነጋዴዎች ያመረቱበት እና ገዝተው የሚሸጡበት የአኩሪ አተር የሽያጭ ዋጋ ካወጡት ወጭ ጋር የተመጣጠነ ስላልሆነ የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲያፈላልግ ጠየቁ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አኩሪ አተር በቋራ ወረዳ በስፋት መመረት ከተጀመረ ሁለት አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የ2013 /2014 ዓ.ም የምርት ዘመን አርሶ አደሮችም ሆኑ ነጋዴዎች ተመጣጣኝ የሆነ ትርፍ በማግኘት ለበለጠ ስራ ተነሳሽ በመሆን በ2014/2015 የምርት ዘመን በርካቶች ወደ እርሻ ስራ መግባታቸው ተመላክቷል፡፡ በወረዳችን በእርሻ ስራ እና በንግድ ስራ የተሰማሩ አቶ ንብረት አብች ፣ አቶ ሞላ ጥላሁን ፣አቶ ብረሃኑ አበበ እና አቶ ዘመነ ባበይ እንዲህ ይላሉ:_ የዛሬ አመቱን የአኩሪ አተር ዋጋ አይተን አንድ ሄ/ር በ8 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ በመከራየት፣ የበሬ ዋጋ ፣ የማሳረሚያ ፣የፀረ አረም፣የማሳ ማሳጨጃ እንዲሁም የመውቂያና የትራንስፖርት ያወጡት ወጭ አሁን ካለው የአኩሪ አተር ገቢያ ጋር መመጣጠን ሳይሆን ለኪሳራ የዳረጋቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተመሳሳይ በንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶችም ምንም እንኳ እንደ አርሶ አደሩ በርካታ ወጭ ባያወጡ በኪሎ 32 ብር የገዙት አኩሪ አተር ዋጋ አሁን 26 ብር በመሆኑ በኩንታል 600 ብር ኪሳራ እንደገጠማቸው ገልፀዋል። በመሆኑም የሚመለከተው አካል አርሶ አደሮች እና ነጋዴዎች የልፋት ዋጋቸውን እንዲያገኙ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ ቋራ ኮሚዩኒኬሽን እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply