በበዓላት ከ105 ሺህ በላይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመርዳት እንቅስቃሴ ተጀመረ

በበዓላት ከ105 ሺህ በላይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመርዳት እንቅስቃሴ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትንሳኤ እና ኢድ አልፈጥር በዓላት ከ105 ሺህ በላይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመርዳት እንቅስቃሴ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ አስታወቀ፡፡
ቢሮው “በጎነት ለጋራ ደስታ” በሚል መሪ ቃል ነው በትንሳኤ ፣ ኢድ አልፈጥር በዓላትና በአርበኞች ቀን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን፣ ጧሪ እና ደጋፊ የሌላቸውን አረጋውያን የሀገር ባለውለታ የሆኑ አርበኞች ለመርዳት እንቅስቃሴ መጀመሩን ያስታወቀው፡፡
የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ፍስሃ ጥበቡ እንደገለጹት በክረምትና በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ከአረጋውያን ቤት እድሳት ጀምሮ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን እና የጎዳና ተዳዳሪዎችን የመደገፍ ስራዎች እየተሰራ ነው፡፡
አጠቃላይ ከ105 ሺህ በላይ አቅመ ደካሞችን ለመርዳት እና ከ150 ቤቶችን ለማደስ ዕቅድ መያዙን አቶ ፍስሃ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ሁሉም በሚችለው አቅሙ የድርሻውን በማበርከት ማህበራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ከለተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በበዓላት ከ105 ሺህ በላይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመርዳት እንቅስቃሴ ተጀመረ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply