በበዓላት ወቅት ህብረተሰቡ ራሱን በፍጥነት እየተስፋፋ ካለው ኮቪድ-19 እንዲጠብቅ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ::ስርጭቱ በፍጥነት እየጨመረ የመጣው የኮቪድ 19 ወረርሺኝን ለመከላከል…

በበዓላት ወቅት ህብረተሰቡ ራሱን በፍጥነት እየተስፋፋ ካለው ኮቪድ-19 እንዲጠብቅ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ::

ስርጭቱ በፍጥነት እየጨመረ የመጣው የኮቪድ 19 ወረርሺኝን ለመከላከል በበዓላት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ፡፡

ኢንስቲትዩቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በዓላትን አስመልክቶ በሚኖሩ የጸሎት ስነ-ስርዓቶች ፣ የእንግዶች መስተንግዶ፣ ግብይትና መሰል እንቅስቃሴዎች ላይ ጥንቃቄን ከማድረግ ባሻገር ህብረተሰቡ ክትባት እንዲወስድና ክትባቱን ከዚህ ቀደም ወስደው ስድስት ወር የሞላቸውም ማጠናከሪያውን እንዲወስዱ አሳስቧል፡፡

ቫይረሱ ላለፉት ሁለት ዓመታት ዝርያውን በመቀያየር የዓለማችን ስጋት ሆኖ ቀጥሏል ያለው ኢንስቲትዩቱ፣ በኢትዮጵያም ባለፉት 7 ቀናት ብቻ ከ27 ሺህ በላይ ሰዎች ኮቪድ-19 እንደተገኘባቸውና 70 የሚሆኑትም ህይወታቸውን እንዳጡ ገልጿል።

ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በአንድ ሳምንት ውስጥ በእጥፍ ጨምሮ 442 መድረሱን አስታውቋል፡፡

የበሸታው ምልክት የታየባቸው ሁሉ አቅራቢቸው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በማምራት ምርመራ እንዲያደርጉና ቫይረሱ ከተገኘባቸውን አስፈላጊውን ህክምና እንዲከታተሉ አሳስቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ታህሳስ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply