ባሕር ዳር: ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በበጀት ዓመቱ የሳይበር ጥቃቶችን በመከላከል 23 ነጥብ 2 ቢልዮን ብር ማዳን መቻሉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አሥተዳደር አስታወቀ፡፡ የአሥተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ላይ ስድስት ሺህ 959 የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝረው 96 ነጥብ ሁለት በመቶውን መመከት ተችሏል፤ ቀሪውም በሂደት ላይ ይገኛል፡፡ […]
Source: Link to the Post