በቡለን፣ በድባጤ፣ ማንዱራ፣ ማንቡክ እና ዳንጉር ወረዳዎች ዛሬም ተጨማሪ የሰው ሕይወት ማለፉን የመተከል ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም…

በቡለን፣ በድባጤ፣ ማንዱራ፣ ማንቡክ እና ዳንጉር ወረዳዎች ዛሬም ተጨማሪ የሰው ሕይወት ማለፉን የመተከል ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም…

በቡለን፣ በድባጤ፣ ማንዱራ፣ ማንቡክ እና ዳንጉር ወረዳዎች ዛሬም ተጨማሪ የሰው ሕይወት ማለፉን የመተከል ዞን ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የክልሉ መንግስት ወንጀል ፈፃሚዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ አለመሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በመተከል ዞን አርቆ የማሰብ የሞራል ልዕልና በሌላቸው አንዳንድ አመራሮችና የጥፋት ኃይሎች ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ከሰሞኑ አብመድ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ በቡለን፣ በድባጤ፣ ማንዱራ፣ ማንቡክ እና ዳንጉር ወረዳዎች ዛሬም ተጨማሪ የሰው ሕይወት ማለፉን በመተከል ዞን ተፈናቃይ አርሶአደሮች ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው ወንጀል ፈጻሚዎች ላይ አሁንም ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ አይደለም ብለዋል፡፡ ሲፈናቀሉ ትተዋቸው የመጡት የቀንድ ቀብቶች ሙሉ በሙሉ እንደተወሰዱባቸውም አርሶአደሮቹ ተናግረዋል፡፡ ወቅቱ ዓመቱን ሙሉ የለፋንበትን ሰብል የምንሰበስብበት ጊዜ በመሆኑ ሰላም ተፈጥሮ ወደ ቀያችን በመመለስ የደረሱ ሰብሎችን መሰብሰብ የምንችልበት ሁኔታ ይፈጠርልን ሲሉም ተፈናቃይ አርሶአደሮች ጠይቀዋል፡፡ ግድያውም ከፓዌ ወረዳ በስተቀር በሁሉም ወረዳዎች ዛሬም እየደረሰ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም እና ህዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ ጋሹ ዱጋዝም አምነዋል፡፡ አቶ ጋሹ ዱጋዝ በመተከል ዞን በሚገኙ ስድስቱም ወረዳዎች አስተማማኝ ሰላም እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እየተሰራ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡ አብመድ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply