በቡለን ወረዳ “በኩጂ ቀበሌ” በተፈፀመው ጥቃት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የከፋ ችግር ውስጥ እንዳሉ ተናገሩ ።            አሻራ ሚዲያ    ታህሳስ፡-…

በቡለን ወረዳ “በኩጂ ቀበሌ” በተፈፀመው ጥቃት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የከፋ ችግር ውስጥ እንዳሉ ተናገሩ ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-…

በቡለን ወረዳ “በኩጂ ቀበሌ” በተፈፀመው ጥቃት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የከፋ ችግር ውስጥ እንዳሉ ተናገሩ ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-17/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር ከመተከል ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ በአጥፊው ቡድን የተፈናቀልን የአማራ ተወላጆች ላይ ብዙ ግፍና በደል እየደረሰብን ይገኛል ሲሉም ተፈናቃዮች ለአሻራ ሚዲያ ገልጸዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ በቤንሻንጉል ታጣቂ ሀይሎችና በኦነግ አባላት ተባባሪነት እንዲሁም በክልሉ የስራ ሀላፊዎች ትዕዛዝ ሰጭነት ምክንያት ቤታቸው እንደተቃጠለባቸውና ንብረታቸውም እንደተዘረፈ ጠቁመው ለዚህ ሁሉ ግድያና የንጹሀን ሞት በክልሉ የሚገኙ የስራ ሀላፊዎች ዋና ተዋኒያን እንደሆኑ ከሞት የተረፉት ነዋሪዎች ጠቁመዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ እንደገለጹት መንግስት አጥፊውን ቡድን በችልተኝነት በማለፉ የጉምዝ ታጣቂ ሀይል ከኦነግ ጋር በመተባበር ስንለፋበት እና ስንደክምበት የቆየነውን ሀብት ንብረት ዘርፏል ፡፡ይህ ደግሞ የመንግስት ድክመት ስለሆነ ለተበደልነው መንግስት ካሳ ይክፈለን ሲሉ ተፈናቃዮች ተናግረዋል፡፡ ከቡለን ወረዳ የተፈናቀሉ ዜጎች እንደተናገሩት ችግር ውስጥ መሆናችንን ለሚመለከተው አካል ብናመለክትም ችግራችንን ሊፈታ የሚችል ምላሽ አላገኘንም ብለዋል፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው በመንግስት ቸልተኝነት ነው ያሉት ተፈናቃዮቹ አሁንም በቤንሻንጉል ክልል አመራሮች ላይ እርምጃ ካልተወሰደ ከዚህ በላይ የከፋ ችግር ሊከሰት ይችላል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም አሁንም ችግር ውስጥ ስላለን የአማራ ክልል መንግስት ሆነ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን ትብብር ያድርግልን ሲሉ ተፈናቃዮች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply