You are currently viewing በቢሾፍቱ ከተማ በ28 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ብሄራዊ የጤፍ ምርምር ቤተ ሙከራ ተመረቀ

በቢሾፍቱ ከተማ በ28 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ብሄራዊ የጤፍ ምርምር ቤተ ሙከራ ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 27 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ሙሉ የገንዘብ ድጋፍ በቢሾፍቱ ከተማ የተገነባው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ብሄራዊ የጤፍ ምርምር የቤተ ሙከራ ህንፃ ተመረቀ።

28 ሚሊየን ብርና ሶስት አመታትን የፈጀው ማዕከል ለተሟላ የምርምርና ጥናት ዘርፍ ተቋሙ ሊያሟላ የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ የኢንስቲቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሰለሞን ጫንያለው ጠቁመዋል።

የብሄራዊ ጤፍ ምርምር ማእከሉ በሚፈለገው የምርምር እና ጥናት አቅም ለመምራት የመሬት ጉዳይ፣ የኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥና ማነስ እንዲሁም የጎርፍ ችግርን የሚመለከተው አካል በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ ተገልጿል።

በምርቃት ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን ህንፃውን ገንብቶ ማስመረቅ በራሱ ግብ ሳይሆን በውስጡ በተለይም በጤፍ ዘርፍ የሚሰሩ የምርምር ስራዎችን መደገፍና በአርሶ አደሩ ዘንድ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት መሰራት እንዳለበት መልእክት አስተላልፈዋል።

ለብሄራዊ ጤፍ ምርምር ቤተ ሙከራው መገንባት ድጋፍ ላደረጉ ተቋሟት እና ግለሰቦች በፕሮግራሙ እውቅና መሰጠቱን ኢቢሲ ዘግቧል።

The post በቢሾፍቱ ከተማ በ28 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ብሄራዊ የጤፍ ምርምር ቤተ ሙከራ ተመረቀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply