በባህላዊ መንገድ የሚካሄደውን የማዕድን ቁፋሮ ማስቆም አልተቻለም ተባለ። በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በባህላዊ መንገድ የሚካሄደውን የማዕድን ቁፋሮዉ ስራ ማስቆም አልተቻለም ተብሏል።የደ…

በባህላዊ መንገድ የሚካሄደውን የማዕድን ቁፋሮ ማስቆም አልተቻለም ተባለ።

በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በባህላዊ መንገድ የሚካሄደውን የማዕድን ቁፋሮዉ ስራ ማስቆም አልተቻለም ተብሏል።

የደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ የማዕድን ስራዎች ፈቃድ መስጠትና ማስተዳደር ቡድን መሪ አቶ በሪሁን አበረ ለጣቢያችን እንደተናገሩት በዞኑ ወደ ሰላሳ የሚደርሱ የተለዩ ቦታዎች እንዳሉ አንስተው ከዚህ ቀደም አደጋ የተከሰተበት ቦታ እና ሌሎቹም ባላቸው ተፈጥሮዓዊ አቀማመጥ ምክንያት ስራ እንዲያቆሙ መጠየቁን ተናግረዋል።

ክረምት መምጣቱን ተከትሎ ከዚህ ቀደም የተከሰቱ መሰል አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ማህብረሰቡ ቁፋሮውን እንዲተው በደብዳቤ ብንጠይቅም እስካሁን ሊቋረጥ እንዳልቻለ አቶ በሪሁን ተናግረዋል፡፡

የአካባቢው ማህበረሰብ በቅርብ የኦፓል ማዕድን ለማውጣት በቁፋሮ ላይ እያሉ ዋሻ የተናደባቸው ሰዎች ከደረሰባቸው አሳዛኝ ገጠመኝ ሳይማር ወደ መደበኛው የኦፓል ማዕድን የማውጣት ስራ እንደተሰማራ ህገወጥ እና ስራውንም ማስቆም እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡

የአካባቢው ማሕበረሰብ ከተፈጠረው አደጋ እንዲማር በደብዳቤ ለሚመለከተው አካል እንዲሁም ለጸጥታ አካላት ብናሳውቅም ቁፋሮው እንዳለቆመ እና በአካባቢው ያለው የጸጥታ ችግርም ድርጊቱን እንዳናስቆም እንቅፋት ሆኖብናልም ብለውናል።

የአካባቢው ማሕበረሰብ ኑሮውን መሰረት ያደረገው ያለምንም መሳሪያ በባህላዊ መንገድ በሚደረግ የኦፓል መአድን ማውጣት ስራ ስለመሆኑ ተነስቷል።

ከዚህ ቀደም የተፈጠረው አደጋም በባህላዊ መንገድ በሚደረገው ሂደት እና በጥንቃቄ ጉለት በመሆኑ ሌላ ህይወት እንዳይጠፋ አሁንም ለሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ እና በመሰል ዘዴዎች ቁፋሮውን ለማስቆም የሚደረገው ጥረት እንዳልተቋረጠ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በተለምዶ ቆቅ ውሀ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የኦፓል ማዕድን ለማውጣት በቁፋሮ ላይ እያሉ ዋሻ የተናደባቸውን ሰዎች ህይወት ለማዳን ሲደረግ የነበረው ጥረት በመቋረጡ የተጎጂ ቤተሰቦች ተስፋ በመቁረጥ እርም ማውጣተኣቸው የሚታወስ ነው፡፡

በለአለም አሰፋ
ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply