በባህርዳር እና ጎንደር ከተማ ትናንት ምሽት የሮኬት ጥቃቶችን የፈፀመው በሽብር ተግባር የተሰማራው ሕወሃት አመሻሹን ወደ ኤርትራ 3 ሮኬቶችን መተኮሱ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳ…

በባህርዳር እና ጎንደር ከተማ ትናንት ምሽት የሮኬት ጥቃቶችን የፈፀመው በሽብር ተግባር የተሰማራው ሕወሃት አመሻሹን ወደ ኤርትራ 3 ሮኬቶችን መተኮሱ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 5 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሽብር ተግባር የተሰማራው ፀረ አማራው ህወሀት በጎንደር እና በባህር ዳር ትናንት ምሽት ሮኬቶችን መተኮሱ ይታወሳል። መንግስትም ህወሀት ጥቃቱን እንደፈፀመ መግለፁን ተከትሎም ህወሀት ሮኬት መተኮሱን አረጋግጧል። የትናንት ምሽቱን ጥቃት በተመለከተ አንድ የባህር ዳር ነዋሪ ብርቱ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡ የጎንደሩ ነዋሪ እንዳሉት ደግሞ 3 ፍንዳታዎች እንደነበሩና አንዱ ሮኬት 3 ጊዜ ሲፈነዳ መስማታቸውን አብራርተዋል፡፡ ፍንዳታው እስከ 20 ኪሎሜትር ድረስ የመንቀጥቀጥ ሁኔታ እንደነበር አመልክተዋል። ከዚህ የበለጠ ሌላ ጥቃት ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ ከመደናገጥ ይልቅ ራሱን መጠበቅ እንዳለበት ነው አስተያየት ሰጪዎቹ የተናገሩት፡፡ ትናንት ምሽት ወደ ባሕር ዳርና ጎንደር ሮኬት መተኮሳቸውንና በዚህም በአውሮፕላን ማረፊያው አካባቢ መጠነኛ ጉዳት መድረሱን አብመድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያን መሰረት አድርጎ ዘግቧል። ከዚህ በተጨማሪም ወደ ኤርትራ ሮኬት እንደሚተኩስ የገለፀው የህወሃት ቡድን ዛሬ ማምሻውን ወደ ኤርትራ ሮኬት ተኩሷል። በአስመራ ከተማ በ3 ቦታ ላይ እንደፈነዳ የተነገረለት ሮኬት በአውሮፕላን ጣቢያ አካባቢ ሳይሆን እንዳልቀረ የተለያዩ ምንጮች ዘግበዋል። የቢቢሲው ጋዜጠኛ ሞውሊድ ሃጂ አብዲ ኤርትራ አስመራ ከተማ ምሽቱን በ3 ሚሳኤል መመታቷን ገልጿል ያለው ቪኦኤ የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር እና አስመራ ኤር ፖርቱ አቅራቢ ጥቃት ሳይደርስ እንዳልቀረ ጋዜጠኛው ስለመጻፉ ገልጧል። ኤርትራን አስመልክተው የሚዘግቡ ሚዲያዎችም “አስመራ” ውስጥ ከፍተኛ ፍንዳታ መሰማቱ ፤ በኃላም ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ እንደነበር ዘግበዋል። የኤርትራ መንግስት ተተኮሰ ስለተባለው ሮኬት እስካሁን የሰጠው ማብራሪያ የለም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply