በባህርዳር ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ ጉዳይ ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር ተወያዩ

በባህርዳር ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ ጉዳይ ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 1 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በባህርዳር ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ ጉዳይ ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።
በወይይቱ ተሳታፊ በዚሁ ወቅት በሰጡት አስተያየት፥ ህወሓት በህዝብ ስም ሲነግድ የቆየ ዘራፊ ቡድን ነው፤ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ህገ ወጥ ተግባር አሳፋሪ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
በለውጡ አድመው ወደ መቐለ የገቡት እና በየቦታው የእነሱን ተልዕኮ አስፈጻሚዎችን በማደራጅት የኢትዮጵያን ህዝብ ለማተራመስ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
በሰሜን ዕዝ ላይ የደረሰው ጥቃት በዓለም ታሪክ ተፈጽሞ አያውቅም ያሉ ሲሆን፥ ህብረተሰቡም ሽብር ለመፍጠር የተላኩ ባንዳዎችን በማጋለጥ የፈሰሰው የወንድሞቻችን ደም እስኪመለስ ድርስ ከፌደራል መንግስት ጎን መቆም አለበት ብለዋል።
ህወሓት ህዝቡን ለመከራ እና ሰቆቃ ከማጋለጡ በተጨማሪ ህፃናትን መልምሎ ለውግያ አቅርቧል፤ ህዝቡን በእጅ አዙር አራጣ እያበደረ ለእንግልት ዳርጓል፣ልጆችም ብድር ለመመለስ ወደ ሱዳን ለጉልበት ስራ እንዲሰደዱ አድርጓል ብለዋል።
ሌላው የባህርዳር ከተማ ነዋሪ ሻምበል ተስፋየ ገ/ኪዳን የአማራ ህዝብ አቃፊ ነው፣ ሞቴም እዚህ ነው፣ ይህን የምናገረው ለማጎብደድ አይደልም በማለት ለአማራ ህዝብ ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል።
” አንድ እግርን ከአማራ ሌላውን ከሕወሓት የሚያድርጉ ሰዎች ሊመከሩ ይገባል” ብለዋል።
ከለውጥ በኃላ ብዙ ችግር የፈጠረው ህወሓት መሆኑን ህዝቡም ሊረዳው ይገባል ያሉት ሻምበል ተስፋዬ፥ በሴራ የተሞላው ዘራፊው ቡድን ደግሞ ለመቐለ ህዝብ ንፁህ ውሃ እንኳን በተገቢ መንገድ ማቅርብ ያልቻለ ቅቤ አንጓች ነው ብለዋል።
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የህዝብ ተሳጥፎ እና አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ በሪሁን መንግስቱ፥
ከለውጡ በፊት የተፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እየተሰራ ባለበት ጊዜ በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመው ጥቃት አሳፋሪ ነው ብለዋል።
ህወሓት መታገል ያለብን በጋራ ነው ያሉት ኃላፊው፥ አሁን እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት ከሕወሓት እና ከፌደራል መንግስት ጋር መሆኑን ሁሉም ሊረዳው ይገባል ብለዋል።
”ፓርቲዎች ያልፋሉ ህዝብ እንደ ህዝብ ይቀጥላል” ያሉት የህዝብ ተሳጥፎ እና አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊው ህብረተሰቡ ከአላስፈላጊ አሉቧልታ ራሱን በማራቅ ከመንግስት ጎን ሊሰለፍ ይገባል ማለታቸውን አብመድ ዘግቧል።

The post በባህርዳር ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ ጉዳይ ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር ተወያዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply