በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ዳግማዊ ምኒሊክ ክፍለ ከተማ የተዘረፉ የኢትዮ ቴሌኮም መሰረተ ልማት ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ዋሉ። ባህርዳር:- መጋቢት 20/2014 ዓ.ም…

በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ዳግማዊ ምኒሊክ ክፍለ ከተማ የተዘረፉ የኢትዮ ቴሌኮም መሰረተ ልማት ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ዋሉ። ባህርዳር:- መጋቢት 20/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ምዕራብ ሪጅን የህግ አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ምህረት እስከዚያ የኢትዮ ቴሌኮም መሰረተ ልማት አውታሮች ላይ ተደጋጋሚ የዘረፋ ወንጀል እየተፈፀመ ማህበረሰቡን ለከፍተኛ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ እየዳረገ ይገኛል ብለዋል። በተለይም ለግንኙነት መረብ አገልግሎት ሰፊ አገልግሎት የሚሰጡና ከውጭ በከፍተኛ በዶላር የውጭ ምንዛሬ የሚገዙ እንደ መዳብ ፣ኩፐር ፣ፋይበርና መሰል ውድ የሆኑ ቁሳቁሶችን በመዝረፍ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሱ መሆኑን ገልፀዋል። በዚህም ከከተማ እስከ ሀገር ያለውን የግንኙነት መረብ ከማስተጓጎል ባለፈ ለፀጥታ እንዲሁም ለልዩ ልዩ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መዳከም ትልቅ ጫና እያስከተለ መምጣቱን ተናግረዋል። ሆኖም ማህበረሰቡ የመሰረተ ልማት ሀብቶችን ሳይሰላች ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን ልዩ ጥበቃ በማድረግ እንዲህ ዓይነቱን አስነዋሪ ወንጀል በመከላከል የተደራጀ ጥበቃ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል። የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አትንኩት አያሌው በከተማችን ባህርዳር በልዩ ልዩ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጡ የመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰውን ዘረፋ በመከላከልና መቆጣጠር ረገድ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች እየታዩ ቢሆንም የፀጥታ ኃይሉ ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ተጨባጭ ለውጥ በማምጣት በኩል አሁንም የሚታዩ ክፍተቶች መኖራቸውን ገልፀዋል። ከዚህም የተነሳ የዘረፋ ወንጀሎች ሙሉ በሙሉ እንዲቆሙ ባለመሆኑ በቀን 19/07/2014 የተለያየ ይዘት ያላቸው የኢትዮ ቴሌኮም የመሰረተ ልማት አውታሮችን በመዝረፍ በቆራሌው ስም በተዘጋጀ ቦታ እንደተከማቹ በቁጥጥር ማዋላቸውን ተናግረዋል። እንዲህ ዓይነት ወንጀሎችን ማህበረሰቡ ከመላው የፀጥታ ኃይልና ፖሊስ ጋር በመተባበር ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት ገልፀዋል። በዚህ ርካሽ የወንጀል ተግባር በመሰማራት በማህበረሰቡ ዘንድ ከባድ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ኪሳራ እያደረሱ ያሉ ዋና ወንጀለኞች በስውር በመሆን የጎዳና ልጆችንና ቆራሌው ሰብሳቢዎችን በመጠቀም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ በመሆኑ የጠበቀ ክትትል ማድረግ ይገባል ብለዋል። #bahirdarcitycommunication ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply